የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ 11 ቢሊየን ዶላር ገቢ አግኝታለች

Jul 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 30/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበችው የ11 ቢሊየን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ፣ ሀገሪቱ ከ1984 እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት 17 ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ካገኘችው አጠቃላይ የኤክስፖርት ገቢ ጋር እኩል መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው፣ የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት የሥራ አፈጻጸምን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ ኢትዮጵያ በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበችው የ11 ቢሊየን ዶላር የወጪ ንግድ ገቢ፣ ሀገሪቱ ከ1984 እስከ 2000 ዓ.ም ባሉት 17 ተከታታይ ዓመታት ውስጥ በድምሩ ካገኘችው አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ጋር እኩል መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ከዕቅዱ በላይ አፈጻጸም የታየበትና በአንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገበው ታላቅ ውጤት የኢትዮጵያውያን የጋራ ድል መሆኑንም ተናግረዋል።

የውጭ ምንዛሬ ገቢ ምንጮችን በዝርዝር ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከአገልግሎት ወጪ ንግድ 9 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር፣ ከውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት 4 ቢሊየን ዶላር ገደማ፣ እንዲሁም ከሬሚታንስ 7 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ከእርዳታና ብድር 5 ቢሊየን ዶላር ገደማ ወደ ሀገር ውስጥ ፈሰስ መደረጉን ጠቁመው፤ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 38 ቢሊየን ዶላር ገደማ የውጭ ካፒታል ፍሰት ማግኘቷን አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026