የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ኢትዮጵያ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የሄደችበት መንገድ ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ነው - ምሁራን

Jul 8, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅማ ፤ ሐምሌ 1/ 2018 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሄደችበት መንገድ ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ መሆኑን ምሁራን ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትላንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማስፋፋትና ለማዘመን ከተያዙ ቁልፍ ዘርፎች መካከል የኢንዱስትሪው ክፍለ-ኢኮኖሚ ዋነኛውና የትኩረት ማዕከል መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከለውጡ በፊት በሀገሪቱ የነበሩ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከ47 በመቶ በታች እንደነበር ጠቅሰው፤ ለዚህም እንደ ፋይናንስ፣ መሬትና የኃይል አቅርቦት ችግሮች በምክንያትነት ይጠቀሱ እንደነበር ገልጸዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍ መንግሥት ልዩ ኮሚቴ በማቋቋም እያንዳንዱን ኢንዱስትሪ በመጎብኘትና ችግሮቻቸውን በየደረጃው ለመፍታት ባደረገው የተቀናጀ ጥረት፣ ቀድሞ የነበሩ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው ዛሬ ላይ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል፡፡

እያደጉ የመጡት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች በርካታ ምርቶችን በሰፊው በማምረት ከውጭ የሚገቡትን ምርቶች በሀገር ውስጥ ከመተካት ባለፈ፣ ወደ ውጭ የሚላከውን መጠን ከፍ አድርገውታል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራን እንደገለጹት፤ መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የሄደበት መንገድ ተጨባጭ ለውጥ እያሳየ ነው።

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር መስፍን መኮንን (ዶ/ር) እንደተናገሩት፤ ባለፉት ዓመታት የውጭ ምንዛሬ እጥረት በትልቅ ተግዳሮትነት የቆየ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ችግሩ በፍጥነት እየተቀረፈ ይገኛል።

አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸውና የማምረት አቅማቸው በየጊዜው እንዲያድግ በተደረገው ጥረት በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል ብለዋል።

አክለውም ኢንዱስትሪዎች የሀገር ውስጥ ምርቶችን በቀላሉና በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ የውጭ ምርቶችን እያስቀሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ለዚህም የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ውጤቶችን ለአብነት በማንሳት በዚህ ሂደት እያደገ የመጣውን የሀገሪቱን የዲጂታል የቴክኖሎጂ አቅም አጋዠ እንደነበርም ገልጸዋል።

በተጨማሪም በምግብ ራስን ለመቻል ግብርናውን አዘምኖ በስፋት የማምረት ስራ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችል መሆኑን በመግለጽ፣ መንግስት በቀጣይ ይፋ ያደረጋቸውና እየሰራባቸው ያሉ ጉዳዮች ከዚህ የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጡ ተናግረዋል።

ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶችን አስቀርቶ በሀገር ውስጥ የማምረት አቅም እያደገ መምጣቱ፣ እንዲሁም የማዳበሪያ ፋብሪካ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ከውጭ የሚገቡ የግብርና ግብዓቶችን ለማስቀረት የታቀደው ስራ ሀገሪቱን ወደፊት ተወዳዳሪ የሚያደርግ መሆንንም አስረድተዋል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ምጣኔ ባለሙያ እና ተመራማሪ አደባ ገመቹ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ እንደ ስንዴ እና ሩዝ ያሉ ሰብሎችን በስፋት በማምረት ከውጭ የሚገባውን ምርት ለመቀነስና ለማስቀረት ስኬታማ ስራዎችን ማከናወኗን ገልጸዋል።

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ለወጣቶችና ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የስራ እድል እና የገበያ ትስስር እየፈጠረ ይገኛል ብለዋል።

ቀደም ሲል በሀገር ውስጥ አይመረቱም ተብለው ይታሰቡ የነበሩ ምርቶች አሁን ላይ በጥራት እየተመረቱ መሆኑን በመጥቀስ ይህም የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችንና ምርቶችን ማበረታታት በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ ተጨማሪ የስራ እድሎችን ይፈጥራል ብለዋል።

ይህ ጥረት በምግብ ምርት ላይ ያለንን የውጭ ሀገራት ጥገኝነት በመቀነስ፣ ሀገራዊ የምግብ ዋስትናን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚረዳ በመሆኑ ኢትዮጵያ ለዚህ ተጨባጭ ስኬት በትጋት እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል፡፡

የፋብሪካዎች መስፋፋትም ለዚህ ግብ መሳካት መሠረት እየሆኑ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026