የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በሀረሪ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል 

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 2/2018(ኢዜአ)፦ በሀረሪ ክልል በ2018 በጀት አመት ከ4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ያሲን አብዱላሂ ገልጸዋል።

ኃላፊው እንደተናገሩት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚታቀዱ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ በተለይም ገቢን በአግባቡ መሰብሰብ ወሳኝ ነው።

በመሆኑም በተጠናቀቀው በጀት አመት የክልሉን ገቢ አሟጦ ከመሰብሰብ አንፃር ዘርፈ ብዙ ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዚህም በአመቱ 4 ቢሊየን 672 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከ4 ቢሊየን 625 ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ፣ የእቅዱን 99 በመቶ ማሳካት መቻሉን ጠቁመዋል።

ከተሰበሰበው ገቢ መካከልም በቀጥታ ታክስ ከ2 ቢሊየን 612 ሚሊየን ብር በላይ፣ ቀጥታ ካልሆነ ታክስ 2 ቢሊየን 211 ሚሊየን ብር፣ ታክስ ነክ ካልሆነ ገቢ ደግሞ ከ275 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን ጠቁመዋል።

እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ደግሞ ከ526 ሚሊየን ብር በላይ የተሰበሰበ መሆኑን ተናግረዋል።

ገቢው ከ2017 ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነፃፀርም ከ1 ቢሊየን 516 ሚሊዮን በላይ ብልጫ እንዳለውም ነው የገለጹት።

በተለይም የውስጥ መናበብን በማሳደግና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት፤ አገልግሎት አሰጣጥን በማሳደግ፤ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራርን መዘርጋቱ፤ ውዝፍ እዳን አሟጦ መሰብሰቡ እና የቅሬታ አፈታት ስርዓትን ማሻሻል ለገቢ አሰባሰቡ መሻሻል እገዛ አንዳደረገ አስረድተዋል።

የታክስ ተደራሽነት ማስፋትና ብቃትና ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ የሰው ኃይል ስምሪትና አመራር መተግበር መቻሉም ሌላው ለገቢው ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ ጉዳይ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአሰራር ስርዓት ላይ የነበሩ መመሪያዎችን በማሻሻል እና ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊነት የመቀየር ስራ በትኩረት መሰራቱ በዓመቱ የታቀደው እቅድ እንዲሳካ አስችሏል ብለዋል።

በ2019 የበጀት በጀት ዓመትም ከግብር ከፋዩና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የተሻለ ገቢ ለመሰብሰብ እና ለተጀመረው ክልላዊና ሀገራዊ የብልፅግና ጉዞ በብቃት ኃላፊነትን ለመወጣት ዝግጅት እየተደረገ ስለመሆኑም አንስተዋል።

በዓመቱ የተከናወነው የገቢ አሰባሰብ እንዲጎለብት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በተለይም ለታማኝ ግብር ከፋዮች፣ የተቋሙ ሰራተኞች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የቢሮው ኃላፊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026