የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ውጤታማነትን አሻሽሏል

Jul 31, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትንና የወጪ ውጤታማነትን ማሻሻሉን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ገለጹ።

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የ2018 በጀት ዓመት የመንግሥት ግዥና ንብረት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድን በተመለከተ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶችና የሀብት አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል።


የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥርዓት ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለፊስካል መረጋጋት፣ ለመንግሥት ወጪ ቅልጥፍና፣ ለግልጽነትና ተጠያቂነት መጠናከር የጎላ ስትራቴጂካዊ ሚና አለው።

የመንግሥት ግዥ የመንግሥት ፖሊሲ ወደ ተግባር የሚቀየርበት፣ የሕዝብ ሀብት በኃላፊነት የሚተዳደርበት፣ የአገልግሎት ጥራትን የሚያሻሽልና ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓትንና የወጪ ውጤታማነትን ማሻሻል አስችሏል ብለዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመንግሥት የኤሌክትሮኒክ ግዥን በማስፋት፣ የግዥ ዝመናን በማጠናከር፣ ሕጎችና አሠራሮችን በማዘመን አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው፤ ተቋማዊ አቅምን ከማጠናከር ባለፈ በመንግሥት ወጪ ላይ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያጠናከሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

መንግሥት ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለውኃ፣ ለመሠረተ ልማት፣ ለዲጂታል ልማትና መሰል ዘርፎች የሚመድበው በጀት በመንግሥት ግዥ ወደ ተግባር፤ የልማት ፖሊሲ ወደ ውጤት የሚቀየርበት መሆኑንም ተናግረዋል።

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን በኤሌክትሮኒክ ግዥ፣ በዲጂታላይዜሽንና በአሠራር ማሻሻያዎች ያስመዘገባቸው ውጤቶች በመንግሥት ወጪዎች ላይ ያለውን ግልጽነትና ተጠያቂነት የሚያጠናክሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመንግሥት ግዥ ላይ የሚሻሻለው እያንዳንዱ ሂደት በዜጎች ሕይወት ላይ ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ መሆን አለበት ሲሉም አስገንዝበዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሪፎርሙ ግብ የፊስካል ሥርዓትን ማጠናከር፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግና የመንግሥት ወጪን ውጤታማ ማድረግ መሆኑን ገልጸው፤ ለግቡ መሳካት የመንግሥት ግዥ ሥርዓቱን ቀልጣፋ፣ ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በ2019 በጀት ዓመት ሁሉም የፌዴራል ተቋማት የሚመሩበት መርህ ትክክለኛነት፣ ጥራትና ወቅታዊነት መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የዲጂታል ሪፎርም የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ይደግፋል ብለዋል።

የዲጂታል ሽግግር አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ በበጀት ዓመቱ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓትን በተሟላ ሁኔታ መጠቀም፣ የመንግሥትን ንብረት በዘመናዊ መንገድ ማስተዳደር እንዳለባቸውም ገልጸዋል።

የመንግሥት ሀብት የሕዝብ አደራ መሆኑን ገልጸው፤ የሕዝብን አደራ በታማኝነት መጠበቅ የሁሉም የመንግሥት ተቋማት የመጀመሪያ ግዴታ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ውጤታማነትን አሻሽሏል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትንና የወጪ ውጤታማነትን ማ...

Jul 31, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026

በአስተዳደሩ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ተደርጓል

ድሬደዋ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በበጀት ዓመቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን የድሬደዋ አስተዳ...

Jul 20, 2026

በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት እየጣለ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2018(ኢዜአ)፦ በመረጃ የተደገፈ ውሳኔ አሰጣጥ በክልሎች መካከል የተመጣጠነ ልማት ከማረጋገጥ አንጻር ጠንካራ መሰረት መጣል መቻሉን የፌ...

Jul 7, 2026