የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

Oct 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) ገለጹ።

በሀላባ ዞን " የመደመር መንግሥት ፤ የሕዝብ ድምፅ ፣ የጋራ ተሳትፎ ፣ የጋራ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የህዝብ ውይይት መድረክ በቁሊቶ ከተማ ተካሂዷል።


ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ለዘላቂ ሰላምና ልማት መፋጠን ማህበረሰባዊ እሴቶችን ጥቅም ላይ የማዋሉ ስራ ይጠናከራል።

የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመኑ ጋር በማጣመር ለሁለንተናዊ የማህበረሰባዊ ለውጥ መረጋገጥ እየተጋ ይገኛል ብለዋል።

ለዚህም "የመልማት ፀጋን ለይቶ ጥቅም ላይ የማዋሉ ስራ ትኩረት ተሰጥቶታል" ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ፤ ለተግባራዊነቱ የወንድማማችነትና የእህትማማችን እሴትን አጎልብቶ መጠቀም ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ መንግስት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል።

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን በበኩላቸው የዞኑ አስተዳደር የማህበረሰቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ተጨባጭ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ ተናግረዋል።


በግብርናው መስክ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በርበሬን ጨምሮ ሌሎች ምርቶችን በስፋት በማምረት ከሀገር አልፎ ለውጪ ገበያ በማቅረብ በዘርፉ የማህበረሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ መጥቷል ብለዋል።

የማህበረሰቡን የሰላም፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

በምክክር መድረኩ ከተሳተፉት መካከል ገራድ ድልታታ ሙዜ እንደገለፁት፤ የመደመር መንግሥት ባጠረ ጊዜ ውስጥ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል።

ሌላኛዋ የምክክር መድረኩ ተሳታፊ እማዋይሽ አምሳሉ፤ መንግስት ማህበረሰቡን የሰላምና የልማቱ አካል እንዲሆን ማድረጉ በቅንጅት እንዲሰራና ውጤታማ እንድንሆን አድርጎናል ብለዋል።

የክልሉ ሰላም መጠበቅና ልማት መጠናከር ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር ባለመሆኑ ህዝቡ ተሳትፎውን ማጠናከሩንም አስረድተዋል።

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎች እንዲጠናከሩ የሚጠበቅባቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

በመርሐ ግብሩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል ፣ የዞንና የቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...

Oct 26, 2026

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026