የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የአቮካዶ ልማትን በማዘመን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ትኩረት ተደርጓል- ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመር

Aug 17, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሐረር፣ ነሐሴ 10/2018 (ኢዜአ)፡- የአቮካዶ ልማትን በማዘመን ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ትኩረት መደረጉን የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድ ሮዛ ኡመር ገለጹ።

ሀገር አቀፍ የአቮካዶ ልማት ኢኒሼቲቭ ከሚተገበርባቸው 10 ክልሎች መካከል አንዱ የሐረሪ ክልል ሲሆን በዛሬው እለትም በገጠርና በከተማ ክላስተሮች የአቮካዶ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል።


የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ኡመር በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የክልሉ መንግሥት በርካታ ኢኒሼቲቮችን ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ነው።

በአሁኑ ወቅትም አቮካዶን ጨምሮ ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ሥራዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

የአቮካዶ ልማት ኢኒሼቲቭ ዋና ዓላማ ምርቱን በቴክኖሎጂ በማዘመን አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር ምርቱን ለውጭ ገበያ ማቅረብን ጨምሮ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የሥራ ዕድል መፍጠር ነው ብለዋል።


በተለይ የክልሉ የአየር ፀባይ ለአቮካዶ ልማት ምቹ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በክልሉ የግብርና ልማት ቢሮ የብሔራዊ የአቮካዶ ልማት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ መሐመድ ሬድዋን ናቸው።

በችግኝ ጣቢያዎች 106 ሺህ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን የማዘጋጀት ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ ችግኞቹን በገጠርና በከተማ በ100 ሄክታር መሬት ላይ ለማልማት መታቀዱን ገልጸዋል።


በችግኝ ተከላው ከተሳተፉት መካከል ወጣት ማሩፋ ሙሳ እና አርሶ አደር አብዲ በያን ፤ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ ያስገኝውን ውጤት መነሻ በማድረግ አቮካዶን ይበልጥ ለማልማት መነሳሳታቸውን ነው የተናገሩት።

አቮካዶ ልማት ሥራ ተጠቃሚነትን ከማጎልበቱ ባሻገር የሥራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ በስፋት እየተሳተፉ እንደሚገኙም ነው ያመለከቱት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12  ባለሀብቶች ላይ  እርምጃ ተወሰደ

ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...

Aug 14, 2026

በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ

ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...

Aug 13, 2026

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ተችሏል 

ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...

Jul 31, 2026

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓት ውጤታማነትን አሻሽሏል

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትንና የወጪ ውጤታማነትን ማ...

Jul 31, 2026