🔇Unmute
(በሙሴ መለሰ)
መሰረተ ልማት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ማዕዘን ከሆኑ ቁልፍ ዘርፎች መካከል የሚጠቀስ ነው። ኢትዮጵያ የነገ ብልጽግናዋን እውን ለማድረግና የዜጎቿን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተፋጠነ መልኩ እየተገበረቻቸው የሚገኙት ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ቁልፍ ሚና አላቸው ።
በመንገድ፣ በባቡር፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች ግንባታዎች ላይ እያፈሰሰች ያለው መዋዕለ ንዋይ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን የሚመጥን የኢኮኖሚ እድገት እና የአኗኗር ዘይቤን በመፍጠር ረገድ ያላቸው አስተዋጽኦም ቀላል አይደለም።
ግዙፉ ፕሮጀክቶቿ መካከልም በጳጉሜን ወር 2017 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለአፍሪካ የኢነርጂ ትስስር ውጥን ትልቅ የምስራች ሆኖ መጥቷል።
የጎረቤት ሀገራት ከግድቡ የሚያገኙት የኤሌክትሪክ አቅርቦት ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያስችላል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙ የሀገራት መሪዎች ባደረጉት ንግግርም በአጽንኦት ያረጋገጡት የህዳሴ ግድብ የአፍሪካ የራስን የመቻል ምልክት እና የኢትዮጵያን አይበገሬነት ተምሳሌትነት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህዳሴ ግድብ ምርቃት ወቅት የተለያዩ ግዙፍ መሰረተ ልማቶች ግንባታ እንደሚጀመር ይፋ አድርገዋል።
የኒውክሌር ኃይል ማበልጸጊያ፣ የጋዝ ፋብሪካ ማስመረቅ፣ የነዳጅ ማጣሪያ እውን ማድረግ፣ በአፍሪካ ግዙፉ አየር ማረፊያ የሆነውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ መጀመር፣ ሁለተኛውን የጋዝ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ማስጀመር እና የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች በመላው ሀገሪቱ ማስጀመር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረጉ ፕሮጀክቶች/የጉባ ብስራቶች/ ናቸው።
በሶማሌ ክልል የጋዝ ፋብሪካ የተመረቀ ሲሆን፣ በአፍሪካ ታሪክ በትልቅነቱ ቀዳሚ የሆነው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በግንባታ ሂደት ላይ ይገኛል።
ይህ ግዙፍ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የሀገሪቱን የሎጂስቲክስና የቱሪዝም አቅም ከመቀየር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የአቪዬሽን መሪነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው።
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሀገሪቱን የግብርና ምርታማነት በዘላቂነት ለመደገፍ ወሳኝ የሆነው የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ እና የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ በየክልሎቹ ካሉ የከተማ ማዘመንና የኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር በተቀናጀ መልኩ ወደ ተግባር እየተሸጋገረ ይገኛል።
በግንባታ ላይ የሚገኘው የኮይሻ የኤሌክትሪክ ኃይል ግንባታም ለኢነርጂ አቅርቦት እድገት የበኩሉን ሚና የሚጫወት ሲሆን፣ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ኢነርጂና የኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ በከፍተኛ ደረጃ ያፋጥነዋል።
እነዚህ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ሀገሪቱ በቅርቡ ከጀመረችው አጠቃላይ የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና የገበያ መር ሥርዓት ጋር የተቆራኙ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ተደርገው ይወሰዳሉ።
የሀገር ውስጥ ምርታማነትንና የዜጎችን የኑሮ ጥራት ከመሰረቱ የሚያሻሽሉ ከመሆናቸውም በላይ፣ ሀገሪቱ በውጭ ዕርዳታና ብድር ላይ ከመደገፍ ወጥታ በሀገር ውስጥ እቅድና አቅም ላይ ተመስርታ የራሷን ዕድል የምትወስን አይበገሬነቷን በተግባር ያሳዩ የኩራት መገለጫዎች ናቸው።
መንግሥት በነዳጅ፣ በጋዝ፣ በማዳበሪያ እና በ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ ላይ የጀመራቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ቀደም ሲል የነበረውን የመንግሥትን ብቻ ፋይናንስ ጥገኝነት በመቀነስ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ የግል ባለሀብቶችን (Private Sector) በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳትፉ አዳዲስ የአጋርነት ሞዴሎችን የፈጠሩ ናቸው።
የተቀናጁ መሰረተ ልማቶች ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን የንግድና የኢኮኖሚ ትስስር በማላቅ ቀጣናዊ ትብብርን ወደ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ ትስስርና በአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነቶች ውስጥ ያላትን ተወዳዳሪነትና ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድጉት አያጠራጥርም።
በመሆኑም እነዚህን ስትራቴጂካዊ የካፒታል ፕሮጀክቶች ከተጀመሩት የከተማ ማዘመንና የኮሪደር ልማት ስራዎች ጋር መተሳሰር፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌትና የኢኮኖሚ ማዕከል አድርጎ ለመገንባት ለተቀመጠው የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ራዕይ መሳካት አስተማማኝ ዋስትና ተደርገው ይወሰዳሉ።
የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያዊያንን የእድገት መሻት ለማሳካት የሚያከናውነው የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው። ለዚህ ስኬት ደግሞ ሁሉም ዜጋ እጅ ለእጅ ተያይዞ በጋራ መንቀሳቀስ ይኖርበታል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገጽ 221 ላይ እንዳመለከቱት አይበገሬነት አንድ አካል ለብቻው የሚወጣው ጉዳይ አይደለም ። ከብዙዎች ጋር ተደምረን የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተግባብተን በመደጋገፍና በመተባበር የምንወጣው ጉዳይ ነው።
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠ...
Aug 13, 2026
ባሕር ዳር ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በሁሉም ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር...
Jul 31, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ግልጽነትና ተጠያቂነት የሰፈነበት የመንግሥት ኤሌክትሮኒክ ግዥ ስርዓትንና የወጪ ውጤታማነትን ማ...
Jul 31, 2026