የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የኢትዮጵያና ሩሲያ የግብርና ንግድ ትብብር የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ የምርታማነት አቅምን ለመገንባት ያግዛል

Oct 14, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያና ሩሲያ የግብርና ንግድ ትብብር የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማሳለጥ የምግብ ዋስትናን የሚያረጋግጥ የምርታማነት አቅም ለመገንባት እንደሚያግዝ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ

በኢዜአ አዘጋጅነት “የሩሲያና የኢትዮጵያ የግብርና ንግድ አጋርነት፤ ኢንቨስትመንት፣ ቴክኖሎጂና የምግብ ዋስትና” በሚል መሪ ሐሳብ የኢትዮ-ሩሲያ የግብርና ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መድረክ ተካሂዷል።

በመድረኩ የግብርና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ማፋጠን፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስርን ማስፋት እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሀገራት የትብብር መስኮች መሆናቸው ተነስቷል።


የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት የሰብል ንግድ ማስፋፊያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዌይሳ ጋረደው፤ የኢትዮጵያ ግብርና የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ረገድ እመርታዊ የዕድገት ጉዞ እያመጣ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ ዕድገት እየተመዘገበ የሚገኘውም በግብዓት፣ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል እንዲሁም በጥናትና ምርምር ታግዞ መሆኑን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው ጠንካራ ግንኙነት የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያግዝ የትብብር ምኅዳር እየፈጠረ መሆኑንም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ የንግድ ተወካይ ያሮስላቭ ታራሲዩክ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሩሲያና ኢትዮጵያ በንግድና በግብርና ልማት ያላቸውን ትብብር እያሳደጉ መምጣታቸውን ገልጸዋል።


ሩሲያ ከኢትዮጵያ ቡናን፣ አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ምርቶችን እንደምትረከብ፣ ኢትዮጵያም ከሩሲያ የአፈር ማዳበሪያና የምግብ ዘይት እንደምታስገባ አስታውቀዋል።

የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በግብርናና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የትብብር ዕድሎችን እያሰፋ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህም የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት መሪ ተመራማሪ ዳርእስከዳር ታዬ፤ የአፍሪካ ዲያስፖራ በሩሲያና በአፍሪካ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር በማጠናከር ጉልህ ሚና እየተወጣ መሆኑን ተናግረዋል።


ዲያስፖራው ያካበተውን ልምድና እውቀት ወደ አፍሪካ በማሸጋገር በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፀደቀ አባተ(ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነትን በማሻሻል የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ አቅሟን እያጎለበተች መሆኑን ገልጸዋል።


በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለው የግብርና ንግድ ትብብርም ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግርን ለማፋጠን ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው አመልክተዋል።

የግብርና ምርቶችን በሀገር ውስጥ የማቀነባበር አቅም ማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን የፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኩባንያ የሀገር ውስጥ ኃላፊ ሀብታሙ ሚሊዮን ገልጸዋል።


ሩሲያ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ያካበተችውን የቴክኖሎጂ አቅም፣ እውቀትና ልምድ ለኢትዮጵያና ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በማጋራት ለዘርፉ ዕድገት የምታደርገውን ድጋፍ ማጠናከር እንዳለባት አሳስበዋል።

የኢትዮ-ሩሲያ የግብርና ትብብር በንግድ ልውውጥ ብቻ ሳይወሰን በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በምርት ማቀነባበር የሀገራቱን የጋራ ተጠቃሚነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026