🔇Unmute
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡
ሀዋሳ ከተማን ሳቢ፣ ምቹና ይበልጥ ተመራጭ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች በርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና በሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተጎብኝቷል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት ከተማዋ ያላት የተፈጥሮ ውበት ይበልጥ ጎልቶ እንዲወጣ የኮሪደር ልማት ሥራው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በአሁኑ ወቅት ግንባታው እየተካሄደ ያለው የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎች ከተማዋን ይበልጥ ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለመዝናኛነት እና ለኮንፈረንስ ምቹና ተመራጭ እንደሚያደርጋት ጠቁመዋል።

እነዚህ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ የክልሉ መንግስት መላውን ህዝብ በማስተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በከተማዋ ለአራተኛ ዙር እየከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ ከጥቃቅን ሥራዎች በስተቀር ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ሥራም በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ በቀን ለ24 ሰዓታት እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።
ለሐይቅ ዳርቻ ልማቱ ህዝቡን በማስተባበር እስካሁን ድረስ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ መቻሉንም ተናግረዋል።
በልማት ሥራዎች ጉብኝት ላይ የሲዳማ ክልልና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...
Oct 10, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...
Sep 15, 2026
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026
ሐረሪ ፤ነሐሴ 7/2018 (ኢዜአ)፦በሐረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ፍቃድ እና መሬት ወስደው ወደ ግንባታና ማምረት ባልገቡ 12 ባለሀብቶች ላይ የኢንቨስትመንት...
Aug 14, 2026