🔇Unmute
አዳማ ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሴራ የተወሰደባትን የባህር በር ለማስመለስ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለዘመናት የቀይ ባህር በር ባለቤት በመሆን አለም አቀፍ ንግድን፣ የባህር ሃይልን እና የጂኦፖለቲካ ተደማጭነትን ስትጠቀም የቆየች ጥንታዊት የባህር ሀገር ናት።
ሆኖም ግን ታሪካዊ ጠላቶቿ በሸረቡት ሴራ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት ብቸኛዋ የባህር በር አልባ የዓለም ሀገር ሆናለች።
ይህም ለውጭ ንግዷ የመሸጋገሪያ እና የሎጅስቲክስ ወጪ እንድታወጣ፣ እንዲሁም ለኢኮኖሚና ለብሔራዊ ደህንነት ተጋላጭነቷ እንዲጨምር አድርጓታል።
በአሁኑ ወቅት ግን ኢትዮጵያ የባህር በር ተደራሽነትን መልሳ ለማግኘት እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ የሀገሪቱን ወቅታዊ የጂኦፖለቲካ እና የቀጣናው ፖለቲካ ሁኔታ የሚያንጸባርቅ ነው።
በጉዳዩ ላይ ለኢዜአ አስተያየት የሰጡት የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በታሪካዊ ስህተት ያጣችውን የባህር በር መብት ለማስከበር የተጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ እና ስትራቴጂካዊ ጥረት ሙሉ በሙሉ ይደግፋሉ።
ይህንን ብሔራዊ ህልም ከግብ ለማድረስ እና የሀገሪቱን የባህር በር ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ማንኛውም እንቅስቃሴ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ድሪባ ጫላ እንደገለፁት ቀይ ባህር የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ነው።
የእኛ ዋና አላማ በሴራ የተነጠቅነውን የባህር በር ማስመለስ ነው ያሉት አቶ ድሪባ፣ እውነታው የቀይ ባህር ተደራሽነት ለትክክለኛ ባለቤቱ ለኢትዮጵያ እንዲመለስ ማድረግ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ጥላሁን ራጎ በበኩላቸው፤ የቀድሞ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት አባል በመሆን በአሰብና ምፅዋ በመኖር የሀገር ዳር ድንበር ሲያስጠብቁ እንደነበር አስታውሰዋል።
የባህር በር ጥያቄ ከግብ እንዲደርስ ከመንግሥት ጎን ሆነን አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።
ያጣነው የባህር በር የሚያስቆጭ ነው ያሉት አቶ ጥላሁን፤ ትውልዱ በሴራ ያጣውን ሀብት ለማስመለስ በቁጭት መነሳቱንም ገልጸዋል።
የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄው፤ ተስፋችን እንዲለመልም ያስቻለ ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ መለሰ አያሌው ናቸው።
ኢትዮጵያ በውስጥና በውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ሴራ የተነጠቀችውን የባህር በር መልሳ እንድታገኝ የተጀመረው እንቅስቃሴና እርምጃ እንዲሳካ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን በማለት አረጋግጠዋል።
ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...
Oct 14, 2026
ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...
Oct 10, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...
Sep 15, 2026
ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...
Aug 27, 2026