የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የመደመር መንግሥት ፕሮጀክቶች በፍጥነት፣ በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ማጠናቀቅ መርሁ ነው

Oct 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ጥቅምት 5/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር መንግሥት የሚያከናውናቸው የልማት ፕሮጀክቶችን በፍጥነት፣ በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ ገደብ አጠናቆ ለአገልግሎት ማብቃት መርሁ መሆኑን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት እና ቤተ-መንግሥት ግንባታን አስጀምረዋል፡፡


ፕሮጀክቱ የመደመር መንግሥትን የሥራ ከባቢን በመለወጥ ደረጃቸውን የጠበቁ ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ርዕይን ማዕከል ያደረገ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ፕሮጀክቱ የክልሉን ሕዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ እሴቶችና የማንነት መገለጫዎች የሚያንፀባርቅ ታሪካዊ አሻራ መሆኑን ገልጸዋል።

በባህር ዳር ከተማ የነበሩትን ታሪካዊ ቅርሶችና አሻራዎች የመጠበቅና የመንከባከብ ሥራዎች መከናወናቸውን ያስታወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ አዲሱ የርዕሰ መስተዳድር ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት የዘመኑን ዕድገትና የአስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ የሚመጥን ሆኖ እንደሚገነባ አስረድተዋል።

በተለይም ፕሮጀክቱ ከጣና ሐይቅና ከዓባይ ወንዝ መነሻ ጋር በተጣጣመ መልኩ ተፈጥሯዊ ውበቱን ጠብቆ የሚገነባ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ጠቅሰዋል፡፡

የመደመር መንግሥት ፕሮጀክቶች በፍጥነትና በጥራት መጠናቀቃቸው ጥብቅ መርህ መሆኑን በመጥቀስ፤ ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜና ጥራት እንዲጠናቀቅ ኮንትራክተሩ፣ አማካሪውና ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026