የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ለሀገር ግንባታ የዜጎች አንድነትና ሁለንተናዊ ቅንጅት መጠናከር አለበት

Oct 22, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 11/2019 (ኢዜአ) ፦የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር የበለጸገች ሀገር ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የዜጎችን ቅንጅታዊ ጥረት ማጠናከር እንደሚገባ በሃዋሳ ከተማ የሚኖሩ አስተያየት ሰጪዎች ገለጹ።

ኢዜአ በሃዋሳ ከተማ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎች፤ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ አጀንዳ የሁሉም እንዲሆን የተጀመሩ ቅንጅታዊ ጥረቶች መጠናከር እንዳለባቸው አንስተዋል።

የትውልዱ ቁጭት የሆነው የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄን ጨምሮ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅሞችን በማስከበር የበለጸገች ሀገር ለመገንባት መላው ዜጋ በቅንጅት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትም ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የታሪክ መምህርና ፖለቲከኛው አቶ በለጠ ስገቦ እንደገለጹት፤ በሃገሪቱ እየተመዘገበ ያለውን ልማት ለማስቀጠል የባህር በር ባለቤት መሆን ጠቀሜታው የጎላ ነው።


የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ከሀገራዊ ልማት ጋር የተያያዘ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን አነስተው፣ የባህር በር ለማግኘት ዜጎች ከመንግስት ጎን በመሆን የጀመሩት ሥራ መጠናከር አለበት ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በዜጎች ተሳትፎ ብሔራዊ ጥቅምን የማስከበር ሥራ ውጤት እያስገኘ በመሆኑ፣ የባህር በር ባለቤት ለመሆን በትውልድ ላይ የሚሰራውን ቅንጅታዊ ሥራ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

የዓለም አቀፍ ታሪክ፣ የቀይ ባህርና ቀጣናው ጉዳዮች ተመራማሪ እንዲሁም የሲዳማ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ወሰንየለህ ስምኦን በበኩላቸው፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማስቀጠል የባህር በር ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ካለበት ቀይ ባህር በሴራ መገለሏና ባህር በር አጥታ እንድትኖር መደረጉ ልማትና ዕድገቷን ለማደናቀፍ በታሪካዊ ጠላቶች የተሰራ ደባ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም በማስቀደም የበለጸገች ሀገር ለመገንባት በመንግስትና በዜጎች የተጀመረው ሁለንተናዊ ጥረት እንዲሳካ በተለያየ መንገድ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።

በተለይ በአሻጥር ሀገር እንድትጎዳ የተደረገበት ታሪካዊና ፖለቲካዊ ስህተት እንዲታረም ከሚሰሩት ሥራ በተጨማሪ የዜጎችን ግንዛቤ የማሳደግ ሚናቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።


ኢትዮጵያ ለዘመናት የቀይ ባህር ወደቦችን የንግድና የውጭ ግንኙነት መስመር አድርጋ ስትጠቀም የቆየች ገናና ሀገር እንደነበረች የገለጹት ደግሞ የልማትና የህዝብ አስተዳደር ባለሙያው አየለ አዳቶ (ዶ/ር) ናቸው።

ምጽዋ፣ አዱሊስ፣ አሰብና ሌሎች የቀይ ባህር ወደቦችን ስትጠቀም የቆየች ሀገር እንደነበረች አስታውሰው፣ በሴራ ምክንያት የባህር በሯን አጥታ ተዘግታ ቆይታለች ብለዋል።

የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ብሔራዊ ጥቅምን ማረጋገጥ ነው ያሉት አየለ (ዶ/ር)፣ ያጣነውን የባህር በር በሰጥቶ መቀበል መርህ መልሶ ለማግኘት የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የሚደገፍ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026

በሀዋሳ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው-ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፣ ነሐሴ20/2018 (ኢዜአ)፡-በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የሐይቅ ዳርቻ እና የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ...

Aug 27, 2026