የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በዞኑ የደረሰው ሰብል ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ በሜካናይዜሽንና በሰው ሃይል በመሰብሰብ ላይ ይገኛል

Oct 28, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዳማ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን የደረሰ ሰብል ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ፣ በሜካናይዜሽንና በሰው ኃይል የተደገፈ የሰብል ስብሰባ በስፋት እየተካሄደ እንደሚገኝ የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የማዕከላዊ ኦሮሚያ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ መስፍን ተሾመ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ በመኸር አዝመራ የለማው ሰብል ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ በፍጥነት ለመሰብሰብ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

በ2018/19 የምርት ዘመን ስንዴ፣ የቢራ ገብስ፣ ጤፍ፣ ሩዝ፣ በቆሎ፣ ቦሎቄና ሌሎች የጥራጥሬ ሰብሎች በዋናነት በዞኑ ከለሙት ሰብሎች መካከል ናቸው።


ሰብሎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ደረጃቸውን በጠበቁ ግብዓቶች ማልማት በመቻሉ እንዲሁም የሙያተኞች ተከታታይ ድጋፍ በመደረጉ፣ የምርት ጥራትን በመጠበቅ በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ሃላፊው ገልጸዋል።

አዳዲስ የምርት ማሳደግያ አሰራሮችና ግብዓት ከመጠቀም ባለፈ ለምርትና ምርታማነት መቀነስ ምክንያት የሆኑ ተባዮችና የሰብል በሽታዎችን በመከላከል ረገድም በዞኑ ውጤታማ ስራ መሰራቱንም ገልጸዋል።

በዞኑ ስንዴ፣ ጤፍና ገብስን ጨምሮ በአብዛኛው ቆላማና ወይናደጋ አካባቢዎች ሰብል ለአጨዳ በመድረሱ፤ ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሽ በኮምባይነር ሃርቨስተርና በሰው ኃይል የመሰብሰብ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

አርሶ አደሩ በደቦና በቤተሰብ ጉልበት የደረሰውን ሰብል በፍጥነት በማንሳት፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በምርት አሰባሰብ ላይ ከሚያሳድረው ተፅዕኖና ጉዳት ራሱን ለመጠበቅ በተቀናጀ ሁኔታ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ዞኑ የማጨጃ ኮምባይነሮችን ከህብረት ሥራ ዩኒየኖችና ከግለሰቦች በተመጣጣኝ ዋጋ በኪራይ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተጨማሪም አርሶ አደሮች በማህበር ተደራጅተው የገዟቸውን ኮምባይነሮች በማቀናጀት የደረሰውን ሰብል የመሰብሰብ ሥራ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል።

በማእከላዊ ኦሮሚያ ዞን በመኸር ከለማው 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ከ130 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅም ጨምረው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...

Oct 26, 2026

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026

በዞኑ በምርት ዘመኑ 28 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት እየተካሄዱ ነው

ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...

Sep 15, 2026