🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን ያሳካችበት መንገድ በራስ አቅም ታላላቅ ልማቶችን ከግብ ማድረስ እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ የቀድሞዋ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ንኮሳዛና ዲላሚኒ ዙማ (ዶ/ር) ገለጹ።
አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቷን በራሷ አቅም እሴት በመፍጠር፣ የምግብ ሉዓላዊነቷን በማረጋገጥ ከውጭ ጥገኝነት መላቀቅ፤ እንዲሁም በዓለም አቀፍ መድረኮች በአንድ ድምፅ መቆም ይኖርባታልም ብለዋል።
ንኮሳዛና ዲላሚኒ ዙማ(ዶ/ር)፤ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ በራስ አቅም ታላላቅ ልማቶችን ከግብ ማድረስ እንደሚቻል የሚያሳይ አስደናቂ ምሳሌ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የውጭ ኃይሎችን በመጠባበቅ ሳይሆን በራሷ አቅምና በዜጎቿ ተሳትፎ የሕዳሴ ግድብን መገንባቷ፣ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ሊከተሉት የሚገባ ተሞክሮ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
በቅርቡ አዲስ አበባን መጎብኘታቸውን ጠቅሰው፤ ከተማዋ በፍጥነት እየተለወጠች መሆኗን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
ይህም በቂ አቅም፣ ቁርጠኝነትና የለውጥ ፍላጎት ሲኖር ብዙ ማሳካት እንደሚቻል የሚያመለክት መሆኑን አብራርተዋል።
አፍሪካ ለግብርና የሚሆን ሰፊ መሬት፣ የፀሐይ ብርሃን፣ ውሃና የሰው ኃይል ያላት በመሆኑ፣ የምግብ ፍላጎቷን በራሷ ማሟላት እንደምትችል አመልክተዋል።
ለዚህም የሚያስፈልገው የአስተሳሰብ ለውጥ፣ የጋራ ቁርጠኝነትና የአገራት ትብብር መሆኑን ገልጸዋል።
ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...
Oct 26, 2026
ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...
Oct 14, 2026
ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...
Oct 10, 2026
ባህር ዳር፤ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ጎንደር ዞን በመኸር ወቅት ከለማው 641 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ከ28 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰ...
Sep 15, 2026