🔇Unmute
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት መሆኑ ይታወቃል። ለዚህ ጀግና እና ህዝባዊ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ምስጋና መስጠት ሲገባ ክህደት ሲፈፀምበት ግን እጅግ አሳዛኝ ነው።ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በባንዳዎች ድንገት የተፈፀመበት ክህደት ታሪክ የማይዘነጋው የክህደት ጥግ ነው።
በመሆኑም የዛሬው እለት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት በባንዳዎች የተፈጸመበትን ታሪካዊ ክህደት እና በጽናት የታለፈበት የሚታወስበት መሆኑ ይታወቃል።

እለቱ ሲታወስ ሰራዊቱ ለአመታት የህዝብን ሰላም፣የሀገር ዳር ድንበር እና የልማት ስራዎችን በሚያግዘው ህዝባዊ ሰራዊት ላይ በውስጥ ባንዳዎች አረመኔያዊ ድርጊትና ታሪክ የማይረሳው ክህደት የተፈፀመበት በመሆኑ የሚዘከርበት ነው።
በዕለቱ የተፈጸመው ድርጊት የትኛውንም ሰብአዊነትና ወታደራዊ ስነ-ምግባር ያልተከተለ የአረመኔያዊ ድርጊት ነበር ማለት ይቻላል። በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለሀገር ክብርና ሉአላዊነት ለዜጎች ፍቅርና አክብሮት ሲል የከፈለው መስዋዕትነት መቼም ቢሆን ሊረሳ አይችልም።

የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን አረመኔያዊ ድርጊት በማውገዝ ከሰራዊቱ ጎን በመሰለፍ መከላከያ ሰራዊት የሀገር ምሰሶ ነው በማለት ከጎኑ በመሰለፍ እገዛና ድጋፉን በተግባር አሳይቷል። ህዝቡ በከሃዲዎቹ ድርጊት በማዘንና በመቆጨት ሀገር ለማፍረስ የተንቀሳሰቀውን የጥፋት ቡድን መመከት ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ወታደራዊ ልብሳቸውን ለብሰው ወደ ግንባር በመዝመት ሀገራቸውን ከጥፋት የታደጉበት አጋጣሚም የዚሁ ታሪክ አካል ነው።
በመሆኑም ጥቅምት 24ን ስንዘክር፣ በዕለቱ ሕይወታቸውን ላጡ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና ዜጎች ክብር በመስጠት፣ እንዲህ አይነት ክህደት ሀገር የማፍረስ እቅድ በመሆኑ እንዳይደገም ትውልድ እያወቀው እንዲሄድ በማድረግ ይሆናል።ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ክብርና ፍቅር በመስጠት ሁላችንም ሀገራዊ አደራችንን መወጣት ይኖርብናል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...
Nov 3, 2026
ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...
Oct 26, 2026
ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...
Oct 14, 2026
ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...
Oct 10, 2026