🔇Unmute
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ሽግግር-የኮፕ32 ተግባራዊ ማሳያ
የብሉምበርግ ጥንክር እንደዘገበው
ዓለም ስለ አየር ንብረት ለውጥ እየተጨነቀና እየመከረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ኢትዮጵያ በተግባር ያሳየችው ድንቅ ውሳኔ የመላው ዓለምን ትኩረት ስቧል።የነዳጅ መኪኖችን ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት በይፋ በመከልከልና ወደ ኤሌክትሪክ መኪና ሽግግር በፍጥነት በመግባት ዓለምን ያስደመመችው ኢትዮጵያ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤት ማስመዝገቧን የብሉምበርግ ጥንክር አትቷል።
በኢትዮጵያ ከሚመነጨው ኃይል 99 በመቶ የሚሆነው ንጹህና አረንጓዴ መሆኑን ያተተው ዘገባው፣ ይህም ለኤሌክትሪክ መኪኖች በርካሽ ኃይል ማቅረብ እንዳስቻላት ገልጿል።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ደግሞ በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱን አመላክቷል። ይህ ታላቅ ሽግግር ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያንም ወጪያቸውን እንዲቆጥቡ አድርጓል ነው ያለው የብሉምበርግ ዘገባ።
የኤሌክትሪክ መኪና የሚጠቀሙ ታክሲ ነጂዎችና የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ቀደም ሲል ለነዳጅና ለጥገና ያወጡት የነበረውን ከፍተኛ ወጪ በማስቀረት በወር እስከ 150 ዶላር (ከ40,000 እስከ 50,000 ብር) መቆጠብ ችለዋል ብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ እንደ ቢኬጂ ግሩፕ ያሉ የመገጣጠሚያ ፋብሪካዎች በሀገር ውስጥ ሥራ በመጀመራቸው፣ በርካታ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎችን በማሰልጠን አዲስ የሥራ እድል መፍጠር ተችሏል።

በኢትዮጵያ በሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ድርሻ 6 በመቶ መድረሱን፣ ይህም ከዓለም አቀፉ አማካይ (4 በመቶ) በላይ በመሆን ኢትዮጵያን በዘርፉ ግንባር ቀደም አድርጓታል።
ኢትዮጵያ በፈረንጆች 2027 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባኤን (COP32) ስታስተናግድ፣ "ታዳጊ ሀገራት በገንዘብ እጥረት ወይም በነዳጅ ቀውስ ሳይገደቡ እንዴት በፍጥነት ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ መሸጋገር ይችላሉ?" ለሚለው ትልቅ ጥያቄ ህያውና በተግባር የተረጋገጠ ማሳያ እንደምትሆንም ነው ብሉምበርግ በዘገባው ያመላከተው።
ኢትዮጵያ እስከ ፈረንጆቹ 2033 አምስት መቶ ሺህ (500,000) የኤሌክትሪክ መኪኖችን በመንገድ ላይ ለማሰማራት የያዘችው ታላቅ እቅድም፣ የዚሁ አረንጓዴ እና ዘላቂ ራዕይ አካል መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...
Nov 3, 2026
ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...
Oct 26, 2026
ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...
Oct 14, 2026
ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...
Oct 10, 2026