የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

በምርጫ ወቅት የምንገባውን ቃል ተግብረን ማሳየት ይኖርብናል-የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች

Nov 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 27/2019 (ኢዜአ):- በምርጫ ወቅት የምንገባውን ቃል ተግብረን ማሳየት ይኖርብናል ሲሉ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ።

2ኛው የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔ "ዕድገትን መምራት ፖለቲካ ፓርቲዎች እንደ የአፍሪካ መጻኢ ኢኮኖሚ መሃንዲሶች" በሚል መሪ ሀሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ መካሄዱን ቀጥሏል።


ኢትዮጵያ በጉባኤው ከመደመር ፍልስፍና የተቀዳውን የፖለቲካ ፓርቲ የለውጥ አስተዳደር ልምዷን አቅርባለች።

ከዚህም ባሻገር በአፍሪካ ምርጫ ከማሸነፍ ወደ ኢኮኖሚ ሽግግር በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የፓናል ውይይት ተደርጓል።

የላይቤሪያ አንድነት ፓርቲ ሊቀ መንበር ሉተር ትራፕህ (ዶ/ር) የሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ወረቀት ላይ ያለ ፕሮግራም መልካም መሆኑን ገልጸዋል።

ነገር ግን ትግበራ ላይ የተለየ መሆኑን ገልጸው፤ ይሄ አይነት አካሄድ መቆም አለበት ብለዋል።

ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ የዜጎችን የኢኮኖሚ ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ አጀንዳ ቀርፆ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልፅ ማሳየቱን ገልጸዋል።


የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር)፤ የምርጫ የመጨረሻ ግብ ሥልጣን መያዝ መሆኑን የለበትም ብለዋል።

የምርጫው ውጤት የዜጎችን ህይወት በመሰረታዊነት የሚያሻሽል የኢኮኖሚ ሽግግር የሚፈጥር መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በመደመር ፍልስፍና እየተመራች ግልጽ ፖሊሲና ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት መሰረታዊ ለውጥ አስመዝግባለች ብለዋል።

የጋና ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ኮንግረንስ ሊቀ መንበር ጆን አሴዱ ንኬቲህ ብልፅግና ፓርቲ የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ የሚመክሩበትን መድረክ በማዘጋጀቱ ምስጋና አቅርበዋል።

በአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ወቅት የምንገባውን ቃል ወደ መሬት ተግብረን ማሳየት ይኖርብናል ብለዋል።

የኢኮኖሚ ፕሮግራሞችን በማጥራት፣ ያለንን የተፈጥሮ ሀብት በመለየት የሚተገበር ርዕዮት መቅረፅ እንደሚገባ ገልጸዋል።

የኮቲዲቯር አይቮሪያን ፖፑላር ፍሮንት ፖርቲ ፕሬዝዳንት ፓስካል አፊ ጉይሳን፤ በምርጫ ያሸነፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሀገራቸውን ኢኮኖሚ ማሸጋገር አለባቸው ብለዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ግልፅና የሀገራቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ከሌላቸው በምርጫ መሳተፍ እንደማይገባቸው ገልጸዋል።

ፓርቲዎች በዜጎች ተጠቃሚነትና ዲሞክራሲ ግንባታ የህዝብን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ርዕዮት ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል።

የቡሩንዲ የዲፌንስ ኦፍ ዲሞክራሲ ብሔራዊ ምክር ቤት ዋና ጸሀፊ ሪቨሪያን ንዲኩሪዮ አፍሪካውያን በትብብር የኢኮኖሚ ፖሊሲ መገንባት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ተዓማኒነት ያለው፣ የሚለካና ሊተገበር የሚችል የፖለቲካ ርዕዮት ዓለም እንዲቀርጹም አሳስበዋል።

አፍሪካ የምኞት ሀይቅ ሆና መቀጠል የለባትም ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ ዕቅዶች ከምኞት አልፈው ገቢራዊ መደረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...

Nov 3, 2026

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...

Oct 26, 2026

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026