🔇Unmute
አዳማ፣ ህዳር 1/2019(ኢዜአ)፡-አርሲ ዩኒቨርሲቲ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለሚያሳድጉ የምርጥ ዘር ብዜት ስራዎች ትኩረት መስጠቱን ገለፀ።
የዩኒቨርሲቲው የግብርናና አከባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ረጋሳ አያና(ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በተግባር ከተደገፈ የመማር ማስተማር ስራዎች በተጨማሪ የአርሶ አደሩን ምርታማነት በሚጨምሩ ተግባራት ላይ እየሰራ ነው።

ዩኒቨርሲቲው የሚሰጣቸው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ችግር ፈቺና የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ እንዲሆኑም የጥናትና የምርምር ስራዎችን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።
በስንዴ፣ በቢራ ገብስ ፣ በጤፍ ፣ በቆሎና አጃን ጨምሮ በድንች ምርቶች ላይም ሰፋፊ የጥናት ምርምር ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በተለይም ከቁሉምሳ ግብርና ምርምር ማእከል ጋር በመተባበር ለአከባቢው የአየር ፀባይ ተስማሚ የሆኑ የስንዴ ፣ገብስና የጤፍ ምርጥ ዘርን ለማውጣት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ1 ሺህ 400 ኩንታል በላይ የስንዴ ምርጥ ዘር በማምረት ለአከባቢው አርሶ አደሮች ተደራሽ ማድረግ መቻሉንም ነው የተናገሩት።
በዘንድሮው ዓመት በ97 ሄክታር መሬት ላይ አባይ ፣ ቢፍቱና ቁሉም የተባሉ የስንዴ ምርጥ ዘርን ጨምሮ ገብስ፣ ነጭና ቀይ ጤፍ ምርት ዘር የማባዛት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል።
በዘንድሮው በጀት ዓመት በስንዴ ምርጥ ዘር ብቻ ከ1 ሺህ 900 ኩንታል በላይ የምርጥ ዘር ለማግኘት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት።
ለእቅዱ ውጤታማነት ከግብርና ምርምር ማእከላት፣ከኦሮሚያ ግብርና ቢሮና ከፌዴራል የግብርና ምርምር ማእከላት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በተለይ ዩኒቨርሲቲው በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን ጥዮና አርሲ ሮቤ ወረዳዎች በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የስንዴ ምርጥ ዘር ብዜት እያከናወነ እንደሚገኝ ጨምረው ገልፀዋል።
በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ እየተከናወነ ያለው የዘር ብዜት ስራ ምርትና ምርታማነት በማረጋገጥ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።
በተመሳሳይ በዘንድሮው ዓመት ዩኒቨርሲው ከ800 ኩንታል በላይ የገብስ ምርጥ ዘር ለማምረት እየሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የስንዴ ፣ ገብስና የጤፍ ሰብል ልማት በጥሩ ሁኔታ ምርት መያዙን ጨምረው ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...
Nov 3, 2026
ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...
Oct 26, 2026
ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...
Oct 14, 2026
ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...
Oct 10, 2026