የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

የሀገር ውስጥ ምርት ስሌትን ማዘመን የኢኮኖሚውን እውነተኛ አቅምና እድገት በትክክል ለመለካት ያስችላል

Nov 11, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ ፤ ህዳር 2/2019 (ኢዜአ) ፦ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌትን ማዘመን የኢኮኖሚውን እውነተኛ አቅም፣ አፈጻጸምና መዋቅራዊ ሽግግር በትክክል ለመገምገም እንደሚያስችል የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ።

የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር የተሻሻለውን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግመታን ወቅታዊ የማድረግ ስራ በይፋ ማሳወቁ ይታወሳል።


በዚህም የተሻሻለው ጠቅላላ የሀገር ውስጥ መረጃ ቋሚ ዓመት ከ2008 ወደ 2017 ዓ.ም እንዲቀየር ተደርጓል።


የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ቋሚ ዓመት ለውጥ ወቅታዊ ግምት መሰረት ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርቱ 59 ነጥብ 2 በመቶ አድጓል።

የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ዘመዴነህ ንጋቱ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ያስመዘገበውን ፈጣን እና ሁለገብ ዕድገት ትክክለኛ መዋቅራዊ ገጽታ ለማሳየት፣ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት መለኪያ ማሻሻያ (Rebased) መደረጉ ተገቢነት ያለው ነው ብለዋል።

ባለሙያው እንደገለጹት፣ ቀደም ሲል ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩት መለኪያዎች የተዋቀሩት ሀገሪቱ በግብርናው ዘርፍ ብቻ ጥገኛ በነበረችበት ወቅት ነው።

በአሁኑ ወቅት የቴሌኮም፣ የፋይናንስ አገልግሎት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ እና የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች እያስመዘገቡት ያለውን ግዙፍ እምቅ አቅም እና አስተዋጽኦ ያላካተቱ በመሆናቸው፣ ወቅታዊውን ሀገራዊ የኢኮኖሚ እውነታ በሚገባ እንደማያሳዩ ተናግረዋል።

ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ያስመዘገቡ ሌሎች የዓለም አቀፍ ሀገራትም ኢኮኖሚያቸውን በዘመናዊ መልኩ መለካት የተለመደ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የደረሰበትን እውነተኛ ዕድገት የሚመጥን እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት መለኪያ ማሻሻያ መደረጉ ተገቢነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም የዘርፉ ምሁራንና ባለሙያዎች በቂ ጊዜ ሰጥተውበት የሚያከናውኑት መሆኑንም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዘርፎችን አፈጻጸም በዘመናዊ መንገድ በመለካት የዕድገት አስተዋጽኦቸውን ለመገምገም እና ትኩረት የሚሹ መስኮችን በቀላሉ ለመለየት የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።

በተለይም ሀገራችን በኢኮኖሚ ልማት እያስመዘገበችው ያለውን እውነተኛ ገጽታ በግልጽ በማሳየት በውጭ ባለሀብቶች ዘንድ ትልቅ መተማመን እንዲፈጠር ያደርጋል ብለዋል።

የሀገራችን የኢንቨስትመንት መስህብነት ከፍ በማድረግ ተመራጭ መዳረሻ እንድትሆን ሰፊ በር የሚከፍት ከመሆኑም በላይ፣ አጠቃላይ የዕዳ ጫናን አቀናጅቶ በመቀነስ ረገድ የጎላ ድርሻ አለው።

የታክስ ሥርዓቱን በማዘመን እና የግብር መሰረቱን ለማስፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...

Nov 3, 2026

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...

Oct 26, 2026

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026