የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ማህበረሰብ እና ባህል

ኢትዮጵያ ጥራቱ የተጠበቀ ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የምትጠቀምበት የጥራት ምዘና ሥርዓት አርዓያ የሚሆን ነው

Nov 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2019(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ጥራቱ የተጠበቀና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የምትጠቀምበት የጥራት ምዘና ሥርዓትና የንግድ እንቅስቃሴው አርዓያነት ያለው መሆኑን ለልምድ ልውውጥ የመጣው የታንዛኒያ ልዑክ ቡድን አባላት ገለጹ።

የኮፊ አረቢካ (ኢትዮፒካ) ቡና መገኛዋ ኢትዮጵያ በልዩ መዓዛና ጣዕማቸው በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርጥ የቡና ዝርያዎችን በማቅረብ ረገድ ቀደምትና ገናና ስም አላት።

ይህም የቡናን ጥራትንና የወጭ ንግድ መጠንን በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ በዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ውስጥ ከፍተኛ የመሪነት ሚና እየተጫወተች ትገኛለች።

ኢትዮጵያ ቡናን በጥሬው የመላክ ልምዷን በመቀየር፣ በአሁኑ ወቅት የቡና ጥራትንና እሴት መጨመርን ማዕከል ያደረገ አሰራረን በመከተሏ ከፍተኛ ገቢ ሊመዘገብ ችሏል።

በዚህም በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፤ በተያዘው በጀት ዓመት ሶስት ወራትም ከ878 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘት መቻሉን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል።

የታንዛኒያ ልዑክ ቡድን አባላት የኢትዮጵያ ምርት ገበያን (ECX) የንግድ እንቅስቃሴ እና የጥራት ማረጋገጫ አሰራር በጎበኙበት ወቅት ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ አጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴዋ የሚደነቅ ነው።


ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል የታንዛኒያ የካፒታል ማርኬትስ ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ንቴሚ ኒሚልዋ ኪለካማጄንጋ እንዳሉት፤ ልዑክ ቡድኑ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የግብርና ምርቶች ዓይነት ብዛት እና የኤክስፖርት ጥራትን በሚያረጋግጠው አካዳሚ በእጅጉ ተደምሟል።

ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ በበለጠ ሰፊ የግብርና ምርቶችን እንደምትገበያይ የጠቆሙት ሰብሳቢው፤ ለአብነትም በአሁኑ ወቅት በታንዛኒያ ምርት ገበያ ያልተካተተውን የበቆሎ ምርትን ጨምሮ በርካታ ለዓለም ገበያ የምታቀርብበት መንገድ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ልዑክ ቡድኑ የኢትዮጵያን ልምድ እንደ ትልቅ ትምህርት የወሰደው ሲሆን፤ በተለይም በታንዛኒያ ምርት ገበያ የሚገበያዩ የግብርና ምርቶችን ዓይነት ማስፋት እንደሚገባ መገንዘቡን ተናግረዋል።

ኪለካ ማጄንጋ አክለውም በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የተቋቋመው አካዳሚ ሌላው የበጎ ተሞክሮ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

የታንዛኒያ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ተቋሙ ለወጪ ንግድ የሚቀርቡ ምርቶች ዓለም አቀፍ የጥራት መስፈርቶችን ማሟላታቸውን እንዴት ማረጋገጥ እንደሚቻል ልምድ የሚቀስሙበት ዕድል እንዳለም ጠቁመዋል።

ከልዑኩ ጋር የመጡት የታንዛኒያ ፋይናንስ ሚኒስቴር ተወካዮችም ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ እንዲህ ዓይነቱን የልምድ ልውውጥ ጉዞ ማመቻቸት በሚቻልበት መንገድ ላይ ፍላጎት ማሳየታቸውን ተናግረዋል።


ሌላኛው ልዑክ ቡድኑ አባል የሕግ ባለሙያው ኤሊያድ ኢ. ምንዴሜ እንደገለጹት፤ ልዑካኑ ምርት ገበያው በተለይም ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚቀርብ ቡናን በጥራት ማረጋገጫ ሥርዓቱ እንዴት እንደሚያሳልፍ በአካል ተመልክተዋል።

ልዑክ ቡድኑ የቡናን ጣዕምና ዝግጅትን መጎብኘቱን ገልጾ፤ በቡና የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓቱ በምርት ገበያው የሚገበያየው ቡና አስፈላጊውን መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን አመልክተዋል።

ይህም ለዓለም አቀፍ ተረካቢዎች በራስ መተማመንን እንደሚፈጥር አብራርተዋል።

በተጨማሪም ይህ ሥርዓት የፋይናንስ ጥቅም እንዳለው ጠቁመው፤ አርሶ አደሮች ከምርት ገበያው የተገኙትን የጥራት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንደ ዋስትና በመጠቀም ከባንክ ብድር ማግኘት እንደሚችሉ መረዳታቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታሪክ የማይዘነጋው ክህደት እና የኢትዮጵያዊያን አኩሪ ጽናት!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሀገርን ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ የልማት አጋር በመሆንና በማህበራዊ አገልግሎት በመሳተፍ ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰራዊት ...

Nov 3, 2026

በክልሉ የመልማት አቅሞችን በመጠቀም የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከናወኑ ተግባራት ይጠናከራሉ

ቁሊቶ ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመልማት አቅሞችን በመጠቀም ዘላቂ ሰላምና ልማትን በማፋጠን የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የሚከና...

Oct 26, 2026

በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራዎች ይጠናከራሉ

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 3 /2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል የህዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ሥራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሳ...

Oct 14, 2026

ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና ትብብር መስራት አለበት-ምሁራን

ጋምቤላ፤ መስከረም 29/ 2019 (ኢዜአ)፡- ሀገራዊ ቀጣይ የልማት ግቦችን ለማሳካት ሁሉም ዜጋ በተደመረ አቅምና በትብብር ሊሰራ ይገባል ሲሉ የጋምቤላ ዩኒቨርሲ...

Oct 10, 2026