የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በመዲናዋ ከ112 ሺህ በላይ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እየወሰዱ ነው

Jan 13, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ጥር 3/2017(ኢዜአ)፡- በአዲስ አበባ ባለፉት ስድስት ወራት ከ112 ሺህ በላይ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እየተከታተሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ 5 ሚሊዮን ዜጎችን የዲጅታል ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የኮደርስ ኢኒሼቲቭ እየተተገበረ ይገኛል።

አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሰጠው ስልጠናም የዳታ ሳይንስ፣ ኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ ሞባይል አንድሮይድና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፎችን ያካትታል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሰለሞን አማረ ለኢዜአ እንዳሉት የኮደርስ ስልጠና በአዲስ አበባ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክትን እውን ለማድረግ ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

በተለይም የዲጂታል እውቀትና ክህሎታቸው ያደገ ሙያተኞችን ለማፍራት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በ2017 በጀት ዓመት እስክ ታህሳስ 30 ድረስ ከ112 ሺህ በላይ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና እየተከታተሉ እንደሚገኙም ገልጸዋል።

ከእነዚህ መካከልም እስከ 30 ሺህ የሚሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን በሚገባ በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ተናግረዋል።

በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በቴክኖሎጂ ሥርዓት እንዲተሳሰሩ መደረጋቸውን ጠቅሰው፥ የኮደርስ ስልጠናው አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ዘመናዊ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።

ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙያተኞች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መሰጠት መጀመሩንም ገልጸዋል።

ሁሉም ቢሮዎች የኮደርስ ኢኒሼቲቭን የሚከታተል ቡድን አቋቁመው እንዲሠሩ እየተደረገ መሆኑንም ጨምረው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026