
ደሴ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፡- የአካባቢያቸውን ሰላም ለማፅናትና ልማትን ለማፋጠን ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አርጡማ ፉርሲ ወረዳ አስያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ።
በህብረተሰቡ ተሳትፎ ሰላምን በማስከበር የልማት ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የወረዳው አስተዳደር አመልክቷል።
በወረዳው የወገሬ ደቢሳ ቀበሌ ነዋሪ አቶ አህመድ አወል ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፤ ሰላማቸውን በመጠበቅ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ሰላምን በማፅናት የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ የአካባቢው አስተዳደር እያደረገ ያለውን ጥረት እንደሚደግፉም ተናግረዋል።

ሌላዋ የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ከድጃ የሱፍ፤ የአካባቢያችን ሰላም በመጠበቁ አሁን ላይ በተለያዩ ተፋሰሶች የአፈርና ውሃ እቀባ ስራ እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል፡፡
የአካባቢያቸውን ሰላም በማፅናት ልማትን ለማፋጠን ድጋፋቸውን በቁርጠኝነት እንደሚያጠናክሩ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል።

ህብረተሰቡን በማሳተፍ የአካባቢውን ሰላም ማስጠበቅ መቻሉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ በትኩረት እንዲሰራ አስችሏል ያሉት ደግሞ የብሔረሰብ አስተዳደር ዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ ናቸው።
ለዚህም ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር በመቀናጀት ሰላም ማስጠብቅ የሚያስችል ውይይትና ምክክር በየጊዜው መካሄዱን ጠቅሰዋል።
ይህም የአካባቢው ሰላም እንዲጠበቅ ምቹ መደላድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
በመሰረት ልማት፣ በመስኖ፣ በሥራ እድል ፈጠራ፣ በበጋ በጎ ፈቃድና በሌማት ትሩፋት ላይ በማተኮር አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ መቻሉንም አብራርተዋል።
የተገኘውን ውጤት ዘላቂ ለማድረግም ህብረተሰቡ አንድነቱን ጠብቆ ሰላሙን ለማጽናት በቁርጠኝነት መስራቱን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ ሥራ በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ እየተከናወነ መሆኑን ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026