የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ

Jun 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2017(ኢዜአ)፦ የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የግብርና ዘርፎች እንዲሳተፉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ጠየቁ።

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በአንጎላ ሉዋንዳ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ አሜሪካ የቢዝነስ ጉባኤ ጎን ለጎን የአፍሪካና የአሜሪካ የግብርና፣ የምግብ እና የቢዝነስ ዘርፍን ለማጠናከር ያለመ የፓናል ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

በፓናሉ ከፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በተጨማሪ የኮትዲቯር ጠቅላይ ሚኒስትር ሮቤርት ቡግሬ ማምቤ እና የኤስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ሚሶ ድላሚኒን ጨምሮ የአሜሪካ፣ የአውሮፓ እና የአፍሪካ ኩባንያዎች ተወካዮች ተሳትፈዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በፓናል ውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት አሜሪካ አሁን ላይ በአፍሪካ ያላትን የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ ያላትን ፍላጎት አድንቀዋል።

አፍሪካ የአሜሪካ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የሚሆን አቅም እንዳላት ጠቅላው በአፍሪካ በኩል ሊለማ የሚችል መሬት፣ የሰው ሃብትና ትክክለኛ ፖሊሲ መኖሩን ማረጋገጥ ይገባል ማለታቸውን ማለታቸውን የኢዜአ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።


በተለይም ጠንካራ የምግብ ሥርዓት መዘርጋት፣ አስተማማኝ የንግድ ትስስር መፍጠርና በምርቶች ላይ እሴት የሚጨምር ቀጣይነት ያለው ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከዚህ አንጻር የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የግብርና ዘርፎች ለመሳተፍ የሚጋብዝ ከፍተኛ አቅም እንዳለ ጠቁመው ይህም በቅርቡ በተግባር ተፈትኖ ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል ብለዋል።

በተለይም በኢትዮጵያ ለእርሻ ሥራ መዋል የሚችል ሰፊ ለም መሬት ያለ መሆኗን ጠቅሰው ይህንን የግብርና ሥራ ሊያከናውን የሚችል የሰው ሀይል ያላት መሆኗንም ገልጸዋል።

አሁን ላይ ኢትዮጵያ በተለይም ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር በተለይም በስንዴ ምርት ላይ በጥቂት ዓመት ውስጥ ከፍተኛ እመርታ ተመዝግቧል ነው ያሉት።

በመሆኑም የአሜሪካ የዘርፉ ተዋናዮች በኢትዮጵያ በተለይም በጥጥ፣ በአቮካዶ እና በስንዴ ምርት ላይ ቢሳተፉ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያላቸውን እምነት ከተጨባጭ አሃዛዊ መረጃ ጋር በማቅረብ አስረድተዋል።

የአሜሪካ ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ኢንቨስትመንት ለረጅም ዓመት የሚዘልቅ መሆን እንዳለበት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026