
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2017(ኢዜአ)፦በ2018 በጀት አመት ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።
የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የኢንተርፕራይዞች ምስረታ እና የሰልጣኞች ምዝገባ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ የማድረግ ሥራ እንደሚቀጥልም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዘርፉ የክልልና ከተማ አስተዳደር አመራሮች የኢንተርፕርነርሺፕ ስልጠና እና ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል።


በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የክልልና የከተማ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች፣ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ እንደተናገሩት፤ ባለፉት አመታት በተቋም ግንባታ፣ በክህሎት ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በአሠሪና ሠራተኛ አበረታች ተግባራት ተከናውነዋል።
የተቋም ግንባታው ሀገር የጀመረችውን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚችል መልኩ መገንባቱን ጠቅሰው፤ የአሠራር ሥራዓቶችን የማሻሻል እና በቴክኖሎጂ የማዘመን ሥራም በትኩረት መሠራቱን ገልጸዋል።
ይህም በ2018 በጀት አመት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።
በክህሎት ልማት ረገድም በተጠናቀቀው በጀት አመት አበረታች ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው፤ የሰው ሀብት ልማት ሥራም ገበያ እና ፍላጎትን መሠረት በማድረግ መሰራቱን ተናግረዋል።
የሥራ እድል ፈጠራ ቁጥር ሪፖርት ጥራቱን የጠበቀ ለማድረግም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ተግባራዊ መደረጉን ገልጸዋል።
ህጋዊ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን ተግባራዊ ለማድረግ፣ ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር ለመፍጠርና ፋይናንስን ጨምሮ አስፈላጊ መንግስታዊ ድጋፎችን ለማቅረብ የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል።
በ2018 በጀት አመት ሁሉም የዘርፉ ተቋማት የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የኢንተርፕራይዞች ምስረታ እና የሰልጣኞች ምዝገባ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የማካሄድ ሥራን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ሚኒስትሯ አስገንዝበዋል።
በሀገር ውስጥ፣ በውጭ ሀገር እና በርቀት ሥራ ዕድል ፈጠራ አበረታች ስራዎች መሰራቱን ጠቅሰው፤ በአዲሱ በጀት አመትም የበለጠ ስኬት ለማስመዝገብ ርብርብ እንደሚደረግ አመላክተዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026