የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በአማራ ክልል ከተሞች በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ አበረታች እድገት እድገት እየተመዘገበ ነው

Jan 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ባህርዳር፤ ታህሳስ 28/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ከተሞች በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ አበረታች እድገት እየተመዘገበ መሆኑን በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የክልሉ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪ የሚመራ የክላስተሩ ቢሮዎች እና ተቋማት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።


የዘርፉ አስተባባሪ አህመዲን መሀመድ(ዶ/ር) እንደገለጹት የክልሉን የ25 ዓመት አሻጋሪ የልማት ዕቅድ መሰረት ያደረገ አደረጃጀት በመፍጠር የክላስተሩ ተቋማት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ እየተሰራ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት በክልሉ በኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና በገቢ አሰባሰብ ዘርፎች አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

የከተማ የኢኮኖሚ ዘርፉ መነቃቃትም ለህዝቡ ምርትና አገልግሎትንበጥራት እንዲሁም በስፋት ማቅረብ እንዳስቻለ ተናግረዋል።


የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ እንድሪስ አብዱ በበኩላቸው የክልሉን እምቅ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የኢንዱስትሪ ዘርፍ የልማት አቅምን የበለጠ ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዚህምባለፉት ስድስት ወራት ከ182 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ከ1ሺህ800 በላይ አልሚ ባለሃብቶች የንግድ ፈቃድ መስጠት መቻሉን ገልጸዋል።

አሰራርን በማዘመንና የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ የክልሉን ኢንዱስትሪ የመልማት ዕምቅ አቅም በአግባቡ ለመጠቀም የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።


የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም ሙሀመድ(ዶ/ር) በበኩላቸውባለፉት ስድስት ወራት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት የሚውል አንድ ነጥብ 3 ሚሊየን ኩንታል የግብርና ምርት ማቅረብ ተችሏል።

ይህምየዘይት ፋብሪካዎችን ጨምሮ ሌሎች አምራች ኢንዱስትሪዎች በአቅማቸው ልክ እንዲያመርቱ ማድረጉን ጠቁመው ግብዓት የማቅረብ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

ከዚህ ጋር በማያያዝም በምርቶች ላይ ባዕድ ነገር በመቀላቀል ለገበያ ለማቅረብ በሚሞክሩ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ እና ነዳጅን በህገ ወጥ መንገድ በሚከዝኑ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱንም ተናግረዋል።

ምርትን በመደበቅና ያለምንም ምክንያት የዋጋ ንረትን ሲያባብሱ በነበሩ 800 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እንደተወሰደም ነው ያስታወቁት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026