የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

Feb 13, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2018(ኢዜአ)፦ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እና በ39ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ።


ዛሬ ንጋት አዲስ አበባ ከገቡት መካከል የጋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሙኤል ኦኩድዘቶ አብላካዋ፣ የሲሸልስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባሪ ፏር፣ የሴኔጋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቸኪህ ናንግ እና የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ሞንደየሰ ሳሚያ ኩምቢያ ይገኙበታል።


በተጨማሪም የኢስዋትኒ የውጭ ጉዳይ እና የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ፎሊል ድላሚኒ ሻካንቱ፣ የቶጎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሮበርት ዱሰይ፣ የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የምስራቅ አፍሪካ ትብብር ሚኒስትር አምባሳደር ማህመድ ታቢት ካምቦ እና የላይበሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ በይሶሎው ኒያንቲ አዲስ አበባ ገብተዋል።

እንዲሁም የኮንጎ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኖይላ ናክዊፓኔ አዬጋናጋቶ በ48ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ እና በ39ኛው የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ከገቡት መከካል ይገኙበታል።

ሚኒስትሮቹ ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሚኒስትሮች የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ለ39ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።


የጅቡቲ፣ የቻድ፣ የጊኒ ሪፐብሊክ፣ የሌሴቶ፣ የኬንያ፣ አልጄሪያ እና ሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትላንት ለሊት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026