የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ኢትዮጵያ እና ቻይና የንግድና የፋይናንስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ እና ቻይና የንግድና የፋይናንስ ትብብራቸውን ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከቻይና ሕዝባዊ ባንክ ገዢ ፓን ጎንግሼንግ ጋር በቤጂንግ ተወያይተዋል።

ውይይቱ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስርን ይበልጥ ለማሳደግ ያለመ ነው።

በውይይቱ ወቅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቡድን 20 (G20) የጋራ ማዕቀፍ ስር ስላለው የኢትዮጵያ የዕዳ ሽግሽግ ሂደት አጠቃላይ ወቅታዊ መረጃ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል።


የኢትዮጵያን ጠንካራ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ዕድገት እንዲሁም የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና የውጭ ምንዛሪ ክምችትን መልሶ ለመገንባት የተከናወኑ ስኬታማ ጥረቶች ተነስተዋል።

የንግድ ልውውጥ ሂደቱን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ እንዲቻል፣ የሁለትዮሽ የገንዘብ ልውውጥ መስመሮችን (Swap lines) ለመዘርጋትና ለንግድ ሥራዎች የሚውሉ የፋይናንስ አማራጮችን ለማስፋት በሁለቱም ወገኖች በኩል ስምምነት ላይ ተደርሷል።

የብሔራዊ ባንክን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ለማጠናከር የቻይናን ገንዘብ (RMB) የመጠቀም አስፈላጊነትን ያነሱት እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ለዚህም እንደ አየር መንገድ ካሉ ተቋማት የሚገኘውን ገቢ መጠቀምና የንግድ ክፍያዎችን ወደ ቻይና ገንዘብ መቀየር እንደ መፍትሔ አስቀምጠዋል።

ይህ ስትራቴጂያዊ እርምጃ የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያላቸውን የሥራ እንቅስቃሴ ከማቀላጠፉም በላይ፣ አዳዲስ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ እንደ ትልቅ ማበረታቻ እንደሚያገለግል አመልክተዋል።

ገዢዎቹ በተጨማሪም የብሔራዊ የክፍያ ሥርዓት መሠረተ-ልማቶችን በማቀናጀት ድንበር ተሻጋሪ ግብይቶችን ዘመናዊ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም መክረዋል።

የቻይና ሕዝባዊ ባንክ ገዢ ፓን ጎንግሼንግ ፓን ጎንግሼንግ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋማት በድንበር ተሻጋሪ የባንኮች የክፍያ ሥርዓት (CIPS) ውስጥ ሊቀላቀሉ የሚችሉባቸውን መንገዶች እና የችርቻሮና የንግድ ክፍያዎችን ለማቀላጠፍ የቻይና ዩኒየን ፔይ (UnionPay) አገልግሎትን ማስፋፋት ስለሚቻልበት ሁኔታ አብራርተዋል።

በተጨማሪም፣ሁለቱም ወገኖች በማዕከላዊ ባንክ ዲጂታል ገንዘብ (CBDC) ልማት ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን፣ የቻይና ሕዝባዊ ባንክ የኢትዮጵያን የዲጂታል ፋይናንስ ዕድገት ለማፋጠን የአቅም ግንባታ እና የልምድ ልውውጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የባንኩ ገዢ ኢትዮጵያ በቅርቡ ያከናወነቻቸውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና የዕዳ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ የወሰደችውን እርምጃ አድንቀዋል።

ሁለቱም ከዓለም አቀፍ የንግድ ልውውጥ እና ከዲጂታል ፋይናንስ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር የሚጣጣም የረጅም ጊዜ እና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አጋርነት ለመቀጠል ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026