🔇Unmute
ወልዲያ፤ መጋቢት 25/2018 (ኢዜአ)፡- የንግድ ትርዒትና ባዛሩ የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት እንዳስቻላቸው የወልዲያ ከተማ ሸማቾች ገለጹ።
ለ"የትንሣኤ ዋዜማ" የተዘጋጀ የንግድና ትርዒትና ባዛር በወልዲያ ከተማ ተከፍቷል።
በንግድ ትርዒትና ባዛሩ ላይ ሲሸምቱ ካገኘናቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ አስናቀች ኃይሌ እንደገለጹት የመጪውን የትንሳዔ በዓል ምክንያት በማድረግ ባዛሩ መከፈቱ የምንፈልገውን ነገር በብዛትና በጥራት ለማግኘት አስችሎናል።
የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶች መቅረባቸውን ጠቁመው በተመጣጣኝ ዋጋ እየተገበያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የዳቦ ዱቄት፣ ዘይትና ሌሎች ምርቶችም በተመጣጣኝ ዋጋ በመቅረቡ ህብረተሰቡ የሚፈልገውን ምርትና የእቃ ዓይነት በጥራትና በብዛት ለማግኘት መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አስረድተዋል።
ሌላዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ ሰናይት አምባቸው በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት ባዛሩ መዘጋጀቱ ለበዓል የሚሆኑ አልባሳትና የመዋቢያ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለመግዛት እንደቻሉም ገልጸዋል።
በባዛሩ የቀረቡት የአገር ውስጥ ምርቶች የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ በመሆናቸው ከውጭ ከሚገቡት ምርቶች የተሻለ ተመራጭነት እንዳላቸውም ተናግረዋል።
የወልዲያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዱባለ አብራሬ ባዛሩን መርቀው ሲከፍቱ እንደገለጹት የንግድ ትርዒትና ባዛሩ አምራቹንና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት ያለአግባብ የሚከሰትን የዋጋ ጭማሪን የሚያስቀር ነው።
ባዛሩ በትንሣኤ በዓል ዋዜማ የተከፈተ በመሆኑ ህብረተሰቡ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት በዓሉን በሰላም ለማሳለፍ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።
የንግድ ትርዒትና ባዛሩ ከመጋቢት 24 እስከ ሚያዝያ 6/2018 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የወልዲያ ከተማ አስተዳደር የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲሱ ወንድሙ ናቸው።
እስካሁን ከክልሉ በተጨማሪ ከኦሮሚያ፣ ከትግራይና ሌሎች አካባቢዎች የመጡ 66 ነጋዴዎች መሳተፋቸውን ጠቁመው ወደ ባዛሩ የሚገቡ ነጋዴዎችና የምርት አቅርቦቱ ሊጨምር እንደሚችልም አስረድተዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026