የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

አገልግሎቱ አሰራርን ከማዘመን ባለፈ  የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ ነው

Jun 16, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልቂጤ፤ ሰኔ 8/2018 (ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰራርን ከማዘመንና ከማቀላጠፍ ባለፈ የአገልጋይነት ባህልን በማዳበር የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በወልቂጤ ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡


ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅቱ እንዳሉት፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግስት ተቋማትን አሰራር ከማዘመን ባለፈ የአገልጋይነት ባህል በመገንባት የተገልጋይ እርካታን የሚያሳድግ ነው።

ለዚህም የአገልግሎት አሰጣጡን በየጊዜው በማዘመንና ተግባሩን በማጥናት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ትኩረት መሰጠቱን አብራርተዋል።

በክልሉ ሦስት ማዕከላት ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸው በክልሉ የመንግስት አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።


የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ በበኩላቸው፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀደም ሲል በተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ የሚስተዋለውን እንግልት በመቀነስ እርካታን እንደሚያመጣ ጠቁመዋል።


በማዕከሉ ሰባት የፌደራልና የክልል ተቋማት 41 የተለያዩ የአገልግሎት አይነቶችን እየሰጡ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ናቸው።


በቴክኖሎጂ የተደራጀው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከዚህ ቀደም ረጀም ቀናትን ይፈጅ የነበረውን ጉዳይ በአጠረ ጊዜ በመጨረስ ፈጣን ምላሽን ይሰጣል ብለዋል።

በክልሉ ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የወልቂጤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሆሳዕናና በወራቤ ከተሞች ከተገነቡት ቀጥሎ ሦስተኛው መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026