የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ዲጂታል የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ትክክለኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎችን ለመቅረጽ ወሳኝ ነው

Jul 15, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬዳዋ፣ሐምሌ6/2018 (ኢዜአ)፡-ዲጂታል የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባን ውጤታማ ማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎችን በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ለመቅረጽ ወሳኝ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጸ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አገልግሎት ጋር በመሆን የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ዲጂታል ሲስተምን በድሬዳዋ አስጀምረዋል።


በማስጀመሪያ ሥነስርአቱ ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት እንደተናገሩት፤ ዲጂታል የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ሥርአትን በተቀናጀ መልኩ መስጠት ተደራሽነትን ያሰፋል።

ዲጂታል የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባን ውጤታማ ማድረግ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎችን በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርቶ ለመቅረጽ ወሳኝ መሆኑንም ገልጸዋል።

በተጨማሪም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ዕቅዶችን አውጥቶ አፈጻጸማቸውን ለመከታተል ጉልህ ጠቀሜታ እንዳለውም አንስተዋል።

የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ዲጂታል አገልግሎት ለስታስቲክስ መረጃዎች ትንተና እንዲሁም ለፖሊሲ አውጪዎች ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት ወሳኝ መሆኑንም ነው ዋና ዳይሬክተሯ ያመለከቱት።


የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው በድሬዳዋና አዲስ አበባ አገልግሎቱ የተጀመረው የሲቪልና ቤተሰብ ዲጂታል አገልግሎት "የዲጂታል 2030" ትግበራ አካል መሆኑን አንስተዋል።

ተግባሩ ቀልጣፋ አገልግሎትን ዕውን በማድረግ የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በላቀ ውጤት ለመፍታት እንደሚያስችልም ገልጸዋል።

ዲጂታል አገልግሎቱ የልደት፣ የጋብቻ፣ የሞት መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመቀመር ለሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ መሳካት ለማዋል በትኩረት ሲሰራ መቆየቱንም አንስተዋል።


የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በበኩላቸው ዛሬ ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በድሬዳዋ ወደ ተግባር የተሻገረው ዲጂታል የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት፣ ለድሬዳዋ ሁለንተናዊ ብልፅግና ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።

የተጀመረውን ዲጂታል አገልግሎት ከመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጋር ተሳስሮ የላቀ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለህዝብ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።

በሥነስርዓቱ ላይ የፌደራል እና የድሬዳዋ አስተዳደር ባለስልጣናት፣ የተቋማት አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026