🔇Unmute
ሰመራ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦በአፋር ክልል አፋምቦ ሐይቅ ላይ በአሳ አስጋሪነት ለተደራጁ ዜጎች የተደረገው ድጋፍ ተጠቃሚነታቸውን እያሳደገው መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች ገለጹ።
የአፋር ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ በአፋምቦ ወረዳ በአራት ማህበራት ለተደራጁ አሳ አስጋሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ወደ ስራ ማስገባቱን ገልጿል።
ተደራጅተው ወደ ስራ ከገቡት መካከል ወጣት ኢብራሂም ሁመድ እንዳለው፤ የተደረገላቸው ድጋፍ በአካባቢያቸው ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ያልዋለውን የአሳ ሀብት አልምተው ተጠቃሚ ለመሆን አስችሏቸዋል።

ይህም በማህበር ተደራጅተው በመስራት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እንዳስቻላቸው ነው የጠቆመው።
የደማአሌ አሳ አስጋሪዎች ማህበር አባል የሆነው ወጣት አብዱ በዱል በበኩሉ፤በተደረገላቸው ድጋፍ የአሳ ምርትን ለሌሎች አካባቢዎች ማቅረብ እንዳስቻላቸው ነው የገለፀው።
የገበያ ትስስርም መመቻቸቱ ጠንክሮ በመስራት ለሌሎች አርአያ እንድንሆን ያግዛል ብሏል።

የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኢብራሂም መሐመድ እንደተናገሩት፤ በክልሉ ባሉ ስምንት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሐይቆች ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ አሳ ልማት ስራ እንዲገቡ ተደርጓል።
ለአብነትም በአፋምቦ ሐይቅ ላይ 200 ወጣቶች በዓሳ ሀብት ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር መዘርጋቱን አስረድተዋል።
የክልሉ ሕብረት ስራ ማኅበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ኤጀንሲ ኀላፊ አቶ አብዱ ሐሰን ያዬ በበኩላቸው፤ በክልሉ ወጣቶችን በማደራጀት ወደ ስራ እንዲገቡ የማድረግ ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

ለዚህም ግብአትና ሙያዊ ስልጠና በመስጠት ገቢያቸውን ከማሳደግ ባለፈ ለህብረተሰቡ ጥራቱን የጠብቀ ምርት ማቅረብ እንዲችሉም አሰፈላጊው ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል ።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026