🔇Unmute
ወራቤ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመንግስት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር የተገልጋይን እንግልት ለመቀነስ ማስቻሉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለፁ።
የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር መድረክ በወራቤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በዚህ ወቅት አቶ አንተነህ እንዳሉት፤ በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመንግስት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር የተገልጋይን እንግልት ለመቀነስ አስችሏል።
ለዚህም በተቋማት ግንባታና በሰው ኃይል ማብቃት ላይ በመሥራት ሰባት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል።
በዚህም በመንግሥት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችን ከመቅረፍ በተጨማሪ የማኅበረሰቡን እርካታ እያሳደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው፤ በክልሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራን ለማሳካት በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የሰው ኃይል ልማት ላይ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ235 ሺህ በላይ ዜጎች ስልጠናውን መውሰዳቸውንና ከእነዚህም ውስጥ ከ185 ሺህ በላይ የሚሆኑት የእውቅና ሰርተፊኬት ማግኘታቸውን አስረድተዋል።
ስልጠናውን ወስደው እውቅና ያገኙትንም የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
በዞኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ ዘርፈ-ብዙ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል ናቸው።

በዞኑ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን የማስፋፋቱ ስራ የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመንና ለወጣቶች የሥራ ዕድልን ለመፍጠር እየዋለ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ይህም የተገልጋዩን ማኅበረሰብ ጊዜ፣ ጉልበትና እንግልት በማስቀረት ረገድ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበበት እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በወራቤ ከተማ ተግባራዊ የተደረገውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ሌሎች የዞኑ መዋቅሮች የማስፋፋት ሥራ ስለመጀመሩም አክለው ገልጸዋል።
ወልቂጤ ፤ሐምሌ 15/2018 (ኢዜአ)፦ በጉራጌ ዞን የመኸር አዝመራን ውጤታማ ለማድረግ ለሰብል እንክብካቤ፣ ለኩታገጠም እርሻና ለግብርና ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ትኩ...
Jul 23, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 14/2018(ኢዜአ)፦ የተፈጥሮ ሀብትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ሥራዎች ለቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ይበልጥ የሚያጎሉ ተግባራት...
Jul 22, 2026
ድሬደዋ፣ሐምሌ 13/2018 (ኢዜአ)፦በድሬደዋ አስተዳደር በበጀት አመቱ ከ71 ቢሊዮን ብር በላይ ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን የአስተ...
Jul 21, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7/2018 (ኢዜአ)፦ መንግሥት የኢትዮጵያን የሎጂስቲክስ ዘርፍ በማዘመን የገቢና የወጪ ንግድን ቀልጣፋ በማድረግ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለማ...
Jul 15, 2026