🔇Unmute
መቱ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ)፡-የአቮካዶ ልማትን በማስፋፋት ምርታማነት እና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን በኢሉባቦር ዞን የበቾ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።
በዞኑ የአቮካዶ ምርትን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የሚደረገውን ጥረት ተከትሎ በአቮካዶ ልማት የሚሳተፉ አርሶ አደሮች ቁጥር እያደገ መምጣቱን የኢሉባቦር ዞን ግብርና ለጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ የዞኑ አርሶ አደሮች መካከል በበቾ ወረዳ የሚኖሩት አቶ ይማም ዓለሙ እንደገለጹት በ2012 ዓ.ም የጀመሩት የአቮካዶ ልማት ሥራ በአሁኑ ወቅት ጥሩ ምርት እያስገኘላቸው ይገኛል።
ይህም የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ አቅም ከመሆን ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እያደረጋቸው መሆኑን ተናግረዋል።
በለፈው ዓመት አስከ 600 ኪሎ ግራም የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ መላካቸውን የተናገሩት አቶ ይማም በተያዘው የምርት ዘመንም ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡትን የአቮካዶ ምርት መጠን ለመጨመር ማቀዳቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የተሻሻሉ የአቮካዶ ዝርያዎችን በስፋት ለማልማት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
የዚሁ ወረዳ አርሶ አደር መሐመድሳሊ ሼህ ሚዝባው ምርታቸውን ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለሽያጭ አቅርበው በሚያገኙት ገቢ ተጠቃሚመሆናቸውንተናግረዋል።
ከአቮካዶ ልማት የሚያገኙትን ጥቅም ለማሳደገም በአሁኑ ወቅት ልማቱን የማስፋፋት ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በተያዘው የክረምት ወራትም እስከ አንድ ሄክታር በሚጠጋ መሬት ላይ ምርጥ የአቮካዶ ዝሪያዎችን በመትከል ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
በወረዳው ለአቮካዶ ልማት ትልቅ ትኩረት በመሰጠቱ በሁሉም ቀበሌዎች ልማቱ እየተስፋፋ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የበቾ ወረዳ ምክትል አክተዳዳሪና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ዲቤሳ ናቸው።

በተለይ ባለፈው ዓመት ከወረዳው የአቮካዶ ምርት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ መቻሉን ተከትሎ በአርሶ አደሩ ዘንድ በአቮካዶ ልማት በስፋት ለመሳተፍ የታየው ተነሳሽነት እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
ልማቱን ለማስፋፋት በተሰጠው ትኩረት በክረምቱ በወረዳው እስከ 100 ሄክታር መሬት ላይ ምርጥ የአቮካዶ ዝርያ ችግኞችን በኩታ ገጠም የማልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል።
ለፍራፍሬ ልማት የተሰጠውን ትኩረት ተከትሎ በዞኑ የአቮካዶ ልማት እየተስፋፋና አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገለጹት ደግሞ የኢሉባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ አወል መሐመድ ናቸው።

በተለይ ባለፈው ዓመት የዞኑ አንዳንድ ወረዳዎች የአቮካዶ ምርትን ለውጭ ገበያ መላክ መጀመራቸው ልማቱን ለማስፋፋት ትልቅ መነሳሳት ከመፍጠሩ በተጨማሪ በመስኩ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ቁጥርም እንዲጨምር አድርጓል ብለዋል።
እስካሁንም በዞኑ 73 ሺህ ሔክታር የሚጠጋ መሬት በአቮካዶ መሸፈኑን የገለጹት አቶ አወል፣ 130 ሺህ የሚደርሱ አርሶ አደሮችም በመስኩ ተሰማርተው እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026