የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት ተከናውነዋል 

Aug 7, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ወልቂጤ፤ ሐምሌ 30/2018 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለጹ።

​​የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል።


የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በክልሉ የመንግሥት ተቋማትን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ሲያቀርቡ እንደገለጹት፣ በበጀት ዓመቱ በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል።

የምርት ማሳደጊያ ግብአትና ዘመናዊ የግብርና አሰራርን በመጠቀም ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በተሰራው ሥራ ውጤት መመዝገቡንም ገልጸዋል።

ለዚህም በክልሉ በሁሉም የምርት ወቅቶች ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ160 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መቻሉን ጠቅሰዋል።

ይህም የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ካለው ጠቀሜታ በተጨማሪ ገበያን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው እንዳሻው (ዶ/ር) ያስረዱት።

በበጀት ዓመቱ ለመስኖ ልማት በተሰጠ ልዩ ትኩረትም የአምስት መስኖ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ሥራ በማጠናቀቅ ከ2ሺህ 300 በላይ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።


በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍም በርካታ ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚ ያደረጉ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ወደ ሥራ እንዲገቡ በመደረጉ ከ379 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ሥራ መፈጠሩን ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በገቢ አሰባሰብ በኩል በተሰራው ጠንካራ ሥራም የክልሉን የውስጥ ገቢ አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ አዎንታዊ ውጤቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ከ27 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ በተሰራው ሥራ 26 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

ገበያን ለማረጋጋት የሚያስችሉ አዳዲስ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎችን ወደ ሥራ ከማስገባት ባለፈ የንግድ ሥርዓቱ በሥርአት እንዲመራ ክትትልና ድጋፍ በመደረጉ ውጤት እየታየ መምጣቱን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026