የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከ2 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀመረ

Sep 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 3/2018 (ኢዜአ)፦ የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በዛሬው ዕለት ከ2 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ አስጀምሯል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ተቋሙ በተለያዩ መልኮች ከነበረበት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ በሪፎርም ወደ ትርፋማ ምዕራፍ መሸጋገሩን ገልጸዋል።

በዚህም ተቋሙ ትርፉን በ42 እጥፍ ማሳደግ መቻሉንና በዛሬው ዕለትም ከ2ሺ 500 በላይ የሚሆኑ ሱቆችን ግንባታ በይፋ ማስጀመሩን ተናግረዋል።


በዛሬው ዕለት የተጀመረው ግንባታ በ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ወጪ በአልሚዎች ትብብር የሚገነባ ሲሆን ባለስድስት ወለል ሕንፃና በቂ የመኪና ማቆሚያ፣ ዘመናዊ መዝናኛ ቦታዎችን ከሱቆች ጋር የያዘ ነው።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በሱቆቹ ለልማቱ የሚነሱት 230 ነባር ተከራዮችን ጨምሮ ተጨማሪ ዜጎች እድል እንደሚፈጠርላቸውም አስታውቀዋል።

ኮርፖሬሽኑ በአንድ ዓመት ውስጥ አስር ህንፃዎችን ለማጠናቀቅ እቅድ መያዙንና ወደ 10 ሺ ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር የሚችሉ ግንባታዎች እየተሰሩ እንደሚገኙም አንስተዋል።

በሌላ በኩል የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በመርካቶ ያስገነባቸውን 399 ሱቆችንም በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026

በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ውጤታማ እያደረገን ነው -ባለሀብቶችና ወጣቶች

ሀረር፤ ነሐሴ 20/2018 (ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል በኢንቨስትመንት ዘርፍ የተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ውጤታማ እያደረጋቸው መሆኑን ባለሀብቶችና ወጣቶች ገለጹ። ...

Aug 27, 2026

የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ

በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመ...

Aug 22, 2026