የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል-የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Sep 14, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣መስከረም 3/ 2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ መስተጋባታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡

አገልግሎቱ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የብሪክስ አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል ብሏል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ስትራቴጂያዊ ድምጾች በብሪክስ መድረክ ተስተጋብተዋል!

ብሪክስ ወደ ሰፊ ጥምረት አድጓል፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አሁን 11 ሙሉ አባላት ያሉት ሲሆን በሩሲያ ካዛን ጉባኤ ይፋ የተደረጉ 10 አጋር አገራትንም በልዩ የአጋርነት ማዕቀፍ በማካተት ተጽእኖውን አጠናክሯል።

የብሪክስ ጥምረት የዓለምን ሕዝብ ቁጥር ግማሽ ያህል፣ የዓለም አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርትን (GDP) 40 በመቶ ገደማ፣ እና የዓለምን ንግድ ሩብ ያህል ይወክላል። መጠኑ እጅግ ግዙፍ ነው። ብሪክስ ከእንግዲህ ተራ ጥምረት ብቻ አይደለም፤ በዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሥርዓት ውስጥ ዋነኛ ኃይል እየሆነ ነው።


የብሪክስ አባል ሀገራት በአለምአቀፍ ደረጃ የተጽዕኖ አድማሳቸው የሰፋ፣ የዓለም አቀፍ የሀብት፣ የቴክኖሎጂ እና የሰፊ ገበያ ማዕከል መዳረሻ ናቸው። የኢትዮጵያ በሳል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ብዙ ሀገራት የሚመኙትን የዚህ ጥምረት አባል የመሆን መሻት እንድታሳካና ተጠቃሚ እንድትሆን አድርጓታል።

በዚህ ሂደት ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ድምፅ በመሆን የአህጉሪቱን ጥያቄዎች እና የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎችን በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች። ከቀሪ የቤት ሥራዎች አንዱ ይህን ታሪካዊ ዕድል በመጠቀም የጥምረቱን ግዙፍ አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ሀብቱ በቀጥታ በሚገኝበት አካባቢ እንዲመረት ማድረግ ነው።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና በማደግ ላይ ባለው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች እውን ለማድረግ ሙሉ ዝግጁነት አላት።


በማዕድን ዘርፍ ኢትዮጵያ ያሏትን እንደ ሊቲየም፣ ታንታለም እና ፖታሽ ያሉ ለዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ እና የኢነርጂ ሽግግር ወሳኝ የሆኑ ሀብቶችን በሀገር ውስጥ በማቀነባበር የኢንዱስትሪ እሴት ሰንሰለቱን ለመቀላቀል ሰፊ ሥራዎችን እየሠራች ይገኛል። ይህ እንቅስቃሴ የሀብት ባለቤት የሆኑ ሀገራት ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወጥተው የተጠናቀቁ ምርቶች አምራች እንዲሆኑ የሚያስችል የጋራ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ይፈጥራል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያላትን ግዙፍ የታዳሽ ኃይል አቅም በመጠቀም አረንጓዴ እና ንጹህ የኢነርጂ አቅርቦትን ለሀገራት ማዳረስ ትችላለች። የውኃ፣ የጂኦተርማል እና የሶላር ኃይል ሀብቶችን በማልማት ለቀጣናው እና ለአጋሮች አስተማማኝ የኃይል ማዕከል ለመሆን የሚያስችል ጠንካራ መሠረት ይጥላል።

ኢኮኖሚያዊ ትስስሩ ከሀብት ማውጣትና ማቀነባበር ባሻገር በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በተቋማዊ ጽናት ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል። የአሠራር ሥርዓቶቻችንን በማጠናከር እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)ን ጨምሮ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የአፍሪካን ልማታዊ እና ማህበራዊ ፍላጎቶች በትክክል እንዲያገለግሉ የጋራ ጥረቶችን ማቀናጀት ያስፈልጋል። ለዚህም ኢትዮጵያ ቁርጠኛ ናት።

ለዘላቂ ዕድገት መረጋገጥ የፋይናንስ ሥርዓቶች ፍትሃዊ መሆን አለባቸው፤ በዚህ ረገድ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የዕዳ ጫና የሚያቃልል አስተማማኝ እና ፍትሃዊ የዕዳ እፎይታ ሒደት ማሳደግ ወሳኝ ነው። የብሪክስ መድረክ የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በመጠቀም ፍትሃዊ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት እንዲዘረጋ ጠንካራ ድምፅ ማሰማት የሚችልበት አቅም አለው።

ከኢኮኖሚ ሽግግር ጎን ለጎን የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከምግብ ዋስትና እና ከዘላቂ ልማት ጋር ማስተሳሰር ይገባል። እንደ ኢትዮጵያ «የአረንጓዴ አሻራ» ተነሳሽነት ያሉ አሠራሮች ለአየር ንብረት ጽናት የሚሰጡትን አስተዋጽኦ በማስፋት የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ ተጨባጭ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ የጋራ ዕድገት ለመለወጥ የሚያስችል ታሪካዊ ዕድል ይፈጥራል። ኢትዮጵያም ይህን ዕድል የአፍሪካ ድምጽ በመሆን ጭምር መጠቀም ጀምራለች ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026

በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ተችሏል

ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...

Sep 7, 2026

በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ ነው

ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...

Aug 31, 2026