🔇Unmute
ዲላ፣ መስከረም 4/2019 (ኢዜአ)፡- በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተያዘው በጀት አመት ቡናን በጥራት እና በብዛት አዘጋጅቶ ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ ከወዲሁ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ገለጸ።
ክልላዊ የቡና ምርት አሰባሰብና ተጓዷኝ ተግባራት ላይ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ዛሬ በዲላ ከተማ ተካሂዷል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ብሩ በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ የቡና አመራረትና ዝግጅት እየተሻሻለ በመምጣቱ ምርታማነትና ጥራትን ማሳደግ ተችሏል።
ከክልሉ በተያዘው 2019 በጀት አመት ቡናን በጥራት በማዘጋጀት በብዛት ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ በየደረጃው በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በበጀት አመቱ ከ48 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማእከላዊ ገበያ እንደሚቀርብ አመላክተዋል።
ጥራት ላለው ቡና የተሻለ ዋጋ መቆረጡ የዘርፉን ተወዳዳሪነት አሳድጓል ያሉት ደግሞ የጌዴኦ ዞን የቡና ላኪዎች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ኢያሱ ወራሳ ናቸው።

ባለፈው ዓመት ቡናን በጥራት ከማዘጋጀት ባለፈ በጊዜ ለገበያ እንዲቀርብ መደረጉ ተጠቃሚነታችን እንዲረጋገጥ አስችሏል ብለዋል፡፡
በተያዘው ምርት ዘመንም ጥራት ያለው ቡና ለገበያ ለማቅረብ ከወዲሁ ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን አመልክተዋል።
ቡና ላኪ አርሶ አደር አሰለፈች ጋን በበኩላቸው የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎችን በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ መቻላቸውን ተናግረዋል።
በተያዘው ዓመትም ከማሳቸው የሚያገኙትን የቡና ምርት በጥራት በማዘጋጀት በቀጥታ የገበያ ትስስር ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በመድረኩ አምራቾች፣ ላኪ አርሶ አደሮች፣ አቅራቢ ነጋዴዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026
ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...
Sep 10, 2026
ባህር ዳር፤ ጳጉሜን 1/2018 (ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የግብርናውን ዘርፍ ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በማስተሳሰር ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የክልሉ ...
Sep 7, 2026
ጋምቤላ፤ ነሐሴ 24/2018 (ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል ለአሳ አጥማጆች የተደረገው የግብአት ድጋፍ አበረታች ውጤት እያስገኘ መሆኑን የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃ...
Aug 31, 2026