የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል-ሰልጣኞች

Apr 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህብረት ስራ ማህበራት አመቻች ባለሙያዎች ተናገሩ።

በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ "ወደ ቀበሌ መድረስ " በሚል መሪ ሃሳብ ለህብረት ስራ ማህበራት አመቻች ባለሙያዎች ላለፉት ስምንት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ስልጠናው ህብረት ስራ ማህበራት ላይ እየተስተዋለ ያለውን የአደረጃጀት ችግር በመቅረፍ በአዲስ መልክ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያደርግ ነው።

ከሰልጣኞቱ መካከል አቶ አምሳሉ ቀነኒ፤ ስልጠናውን ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የዘርፉ ባለሙያዎች መውሰዳቸው ዘርፉን ለመለወጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ነው የገለጹት።


በህብረት ስራ ማህበራት ላይ የሚታዩ የአደረጃጀት እና የፋይናንስ አቅርቦት ችግሮችን በማስተካከል ጠንካራ እና ራሳቸውን የሚያስተዳድሩ ማህበራትን ለመፍጠር እንደሚረዳም እንዲሁ።

በተጨማሪም ማሕበራቱን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ በተሻለ መንገድ በቀጥታ ተሳታፊ ለማድረግም ሰፊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው የተናገሩት።

በወሰዱት ስልጠና መሠረትም የህብረት ስራ ማህበራቱ በአዲሱ ሪፎርም መሠረት ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግና አዳዲስ አሰራሮችን ለመተግበር እንደሚሰሩም ነው ያረጋገጡት።


ስልጠናው መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራትን አሁናዊ ቁመና ከመዳሰስ ባለፈ ኢኮኖሚውን ከማረጋጋት አንፃር ያለውን ክፍተት አሳይቶናል ያሉት ደግሞ ሰልጣኝ አዚዛ አደም ናቸው።

የሂሳብ አያያዝ፣ አደረጃጀት እንዲሁም የድጋፍ እና ክትትል ስራዎችን የበለጠ በማጠናከር የህብረት ስራ ማህበራት ሪፎርሙን እንዲተገብሩ የሚያደርግ በመሆኑም ለስኬታማነቱ እንሰራለን ብለዋል።

ስልጠናው የህብረት ስራ ማህበራትን አደረጃጀትን በማዘመን እና ከነበሩበት የቆየ አሰራር በማላቀቅ ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዛል ያሉት ደግሞ ማሊክ ዩሱፍ ናቸው።


የህብረት ስራ ማህበራት ለህብረተሰቡ ቅርብ በመሆናቸው መሠረታዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ተልዕኳቸውን እንዲወጡ እንሰራለን ነው ያሉት።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሬትና ህብረት ስራ ማደራጃ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኑረዲን ሙክታር በበኩላቸው፤ ሪፎርሙ የህብረት ስራ ማህበራት ብቁ የሰው ሀይል በመያዝ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ እንዲሆኑ የሚያደረግ ነው ብለዋል።


በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው ይህ የህብረት ስራ ማህበራት ንቅናቄ ውጤታማ እንዲሆን አመቻች ባለሙያዎች ያገኙትን ስልጠና በመተግበር ተጨባጭ ለውጥ ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

በስልጠናው ላይ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና አጎራባች ኦሮሚያ ክልል የተውጣጡ ከ4 መቶ በላይ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026