🔇Unmute
አሶሳ፤ ግንቦት 11/2018 (ኢዜአ)፦ የግብርናውን ዘርፍ በምርምር በመደገፍ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ አሰራሮች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ገለጸ።
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ባካሄደው 11ኛው ዓመታዊ የምርምር ኮንፍረንስ ላይ የኢትዮጵያ ግብርና ኢንስትቲዩት በምርምር የታገዙ የግብርና ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬው ተገኝ (ዶ/ር) ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ አብራርተዋል።
ኢንስቲትዩቱ የየአካባቢውን ስነ ምህዳር የሚላመዱ እና በምርምር የተደገፉ የግብርና ውጤቶች ለአርሶአደሩ በሰርቶ ማሳያ መልክ እንዲቀርቡ በማድረግ ላይ መሆኑንም ዶክተር ፍሬው ተናግረዋል።
አርሶአደሩ የእርሻ ማሳውን በቴክኖሎጂ ታግዞ በስፋት እንዲያለማ በማድረግና የግብርናው ዘርፍ ገበያ ተኮር እንዲሆን በተከናወነው ስራም የአርሶአደሩ ህይወት እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ በሁሉም አካባቢዎች በፈጠራ የታገዙ የግብርና ፕሮጀክቶችን ለማከናወን የሚያስችል ማዕከላትን በመክፈት በተለያዩ የሰብል አይነቶችና የእንስሳት ዝርያዎች ላይ የምርምር ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።
በተለይም በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የግብርና ሽግግር ፍኖተ ካርታ የግብርናው ዘርፍ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ የሚያደርግ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ የምርምር ተቋማት እና የግብርናው ዘርፍ አጋር አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አስታውቀዋል።
በግብርና ሽግግር ፍኖተ ካርታው ተጠቃሚ ከሚሆኑት አካባቢዎች አንዱ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መሆኑን የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ ፍኖተ ካርታው በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የግብርና ስራ የበለጠ ውጤታማ በማድረግ የአርሶአደሩን ተጠቃሚነት እና ምርታማነት እንደሚያሳድግ አብራርተዋል።
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ የሚገኘው የምርምር ስራም ለሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተሞክሮነት የሚጠቀስ መሆኑን ዶክተር ፍሬው ጠቅሰዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026