🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሰኔ 16/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ በምግብ ራስን የመቻል ግብን ለማሳካትና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል ፈጣን የምርታማነት ሽግግር ላይ እንደምትገኝ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስትቲዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ሀሳብ የ“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ በሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ የግብርና ዘርፍ የለውጥ ጉዞን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ በዘርፉ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ፣ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ጉልህ ማሻሻያዎችን ማከናወኗን ጠቅሰዋል።
በዚህም የሀገሪቱን የግብርና ዘርፍ ከነበረበት ከእጅ ወደ አፍ ልምምድ በማላቀቅ አሁን ላይ ከእርሻ ወደ ንግድ እና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ወደሚያስችል ጠንካራ መሠረት እየተሸጋገረ ነው ብለዋል።
ለዚህም ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣሙ ስትራቴጂዎችንና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በመንደፍ፤ የመንግሥት፣ የግል ዘርፉንና የህዝብ አጋርነትን ለማጠናከር፣ ፈጠራንና የግብርና ቢዝነስን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የግብርናው ዘርፍ ይበልጥ ምርታማ፣ በገበያ መር እና ለተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ተፅዕኖዎች የማይበገር የምርታማነት ሥርዓት እየተገነባ መሆኑን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኛ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶችን በማስፋት ተጨባጭ ውጤቶች በማምጣት ታሪኳን እየቀየረች ነው ብለዋል።
በስንዴ ምርት ራሷን ከመቻል አልፋ በአፍሪካ ቀዳሚዋ አምራች ሀገር መሆኗንም ተናግረዋል።
የሌማት ትሩፋትና መሰል በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፉ ሀገር በቀል ተነሳሽነቶችን በማዳበር፣ ቴክኖሎጂንና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም የግብርና ምርታማነት እያደገ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በግብርናው ዘርፍ የተወሰዱ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ለዘላቂ የግብርና ልማት፣ ለገጠር ብልጽግና እና ለጠንካራ ኢኮኖሚ መሰረት መጣላቸውን ገልጸዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ወደፊት እየተራመደችና ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበች መሆኑን በተግባር እንደሚያሳይ አመልክተዋል።
የግብርናው ዘርፍ ማሻሻያ የዘርፉን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ማሳደጉን ተናግረዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026