የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ያስመዘገበችው እመርታ የአፍሪካን ኢኮኖሚ ትንሳኤ የሚያበስር ነው - ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ

Jun 24, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 17/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ያስመዘገበችው እመርታ የአፍሪካን ኢኮኖሚ ትንሳኤ የሚያበስር መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በምክትል ዋና ጸሐፊ ማዕረግ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ሀሳብ የ”ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል።

በመንግሥታቱ ድርጅት በምክትል ዋና ጸሐፊ ማዕረግ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴቴ፤ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያስተናገደች ትገኛለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ ግን ዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታ ያልበገረው ፈጣን ዕድገት የምታስመዘግብ አፍሪካዊት ሀገር ለመሆን መብቃቷን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትም የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያና የቁርጠኛ አመራር ውጤቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ እና ዘላቂ የልማት መርሃ ግብሮችም ተምሳሌታዊ መሆናቸውን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያውያን ትብብር የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካ ግዙፉ የታዳሽ ኃይል መሠረተ ልማት መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ የውሃ፣ ነፋስ፣ ፀሐይ፣ ጂኦ ተርማል የታዳሽ ኃይል መሠረተ ልማት ስኬትም ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በማሳለጥ ከፍተኛ ውጤት እያስገኘ ነው ብለዋል።

አፍሪካ ለዓለም አቀፍ ችግሮች የመፍትሔ አካል እንደምትሆን ኢትዮጵያ በተግባር እያሳየች ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ በንጹሕ የትራንስፖርት አማራጭም የአፍሪካ ተምሳሌት መሆን ችላለች ብለዋል።

በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪም አፍሪካን ከዓለም የንግድና ኢንቨስትመንት ምኅዳር በማስተሳሰር ግንባር ቀደም ሚናዋን እየተወጣች እንደምትገኝ አስረድተዋል።

በግብርናው መስክም ከዓመታት በፊት ከፍተኛ የስንዴ ምርት አስመጭ ከነበሩ የአፍሪካ ሀገራት ተርታ የነበረችው ኢትዮጵያ አስደማሚ ስኬት ማስመዝገቧን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የስንዴ ፍላጎቷን በራሷ ከማሟላት ባለፈ ለጎረቤት ሀገራት መላክ መጀመሯ ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ በስንዴ ምርት ራሷን መቻል የአፍሪካን ኢኮኖሚ ትንሳኤ የሚያበስር መሆኑን ጠቅሰዋል።

በቱሪዝም መስክም በቅርስ ጥበቃና ጥገና እንዲሁም አዳዲስ የመዳረሻ ስፍራዎችን በማልማት በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ተደማሪ አቅም እየገነባች መሆኗን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ጠንካራ ዕድገት ማስመዝገቡን ቀጥሏል ያሉት ዋና ጸሐፊው፤ ይህም በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር የመጣ ውጤት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026