የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የሩዝ ልማት ምርታማነትን በማሳደግ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ አድርጓል

Jul 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

መቱ ፤ ሐምሌ 2/ 2018(ኢዜአ):- የሩዝ ልማት ስራ ላይ መሳተፋችን ምርታማነትን በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ አስችሎናል ሲሉ በኢሉባቦር ዞን የዳሪሙ ወረዳ አርሶ አደሮች ተናገሩ።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሩዝ ልማት ስራ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ የመጣና አገሪቱ በምግብ ራሷን ለመቻል በምታደርገው ጥረት ውስጥ እንደ አዲስ ስትራቴጂካዊ ሰብል እየታየ ያለ ነው።

መንግስት በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አካባቢዎች ለሩዝ ልማት ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም እና በዘርፉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከውጭ የሚገባውን ምርት ለመተካት ሰፊ ትኩረት ሰጥቷል ።

በዞኑ የዳሪሙ ወረዳ ቤና 3 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ኑረዲን ኡስማን፣ አህመድ ሁሴን እና ኢብሳ አሊዩ ለኢዜአ እንዳሉት ፤በኩታ ገጠም ሩዝን በማልማት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው አድጓል።


በተለይ ሜካናይዝድ በሆነ መንገድ የሩዝ ልማቱን በትራክተር እና በኩታ ገጠም እርሻ ለማልማት መቻሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዳገዛቸው ነው የገለጹት።

ለሩዝ ልማት ስራ ትኩረት በመሰጠቱና ከራሳችን አልፎ ለገበያ የሚቀርብ ምርት በማስገኘቱ በተሻለ መንገድ ተጠቃሚ ለመሆን አስችሎናል ብለዋል።

በቀጣይ ጊዜያትም የሩዝ ልማት ስራውን ከፍ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።

የዳሪሙ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ታሪኩ ኢታና በበኩላቸው፤ በወረዳው የመኽር እርሻ 128 ሺ ሔክታር መሬት ላይ ሩዝን በማልማት ከ4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል።


በሩዝ ልማቱ ከ172 ሺ በላይ አርሶ አደሮች የሚሳተፉ ሲሆን ከ56 ሺህ ኩንታል በላይ የምርት ማሳደጊያ ማዳበሪያ ጥቅም ላይ እንደሚውልም ገልጸዋል።

የኢሉባቦር ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ ታከለ በበኩላቸው፤ በዞኑ የግብርና ልማትን ስኬታማ ለማድረግ አርሶ አደሩ በወቅቱ ግብአት እንዲቀርብለት ከማድረግ ባለፈ አርሶአደሮች የባለሙያዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።


በመኽሩ ወቅት በሚካሔደው የሩዝ ልማት ስራ 230 ሺ ሔክታር መሬት በማልማት ከ9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን አንስተዋል ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026