የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በዞኑ ከሁለት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአትክልት እና ፍራፍሬ ተሸፍኗል

Jul 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ነቀምቴ፣ሐምሌ 11/2018 (ኢዜአ)፡-በምስራቅ ወለጋ ዞን ከ ሁለት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በአትክልት እና ፍራፍሬ መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የምስራቅ ወለጋ ዞን የአትክልት እና ፍራፍሬ ባለሙያ አቶ ታከለ መኮንን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ በአትክልት እና ፍራፍሬ ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ ነው።

በተለይ በአቮካዶ፣ ሙዝ፣ ማንጎ ፣ እና ፓፓያ ምርት ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራቱ ውጤት ያስገኘ በመሆኑ አርሶ አደሩን ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

ለአብነትም በ2018 የምርት ዘመን 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ኩንታል በላይ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ለማምረት ታቅዶ ከእቅድ በላይ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ተችሏል ነው ያሉት ።

በዘንድሮው አመት በክላስተር እና በመደበኛ ከሁለት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በላይ በፍራፍሬ እና አትክልት መሸፈን መቻሉን ገልጸዋል።

በዞኑ በፍራፍሬ እና በአትክልት ልማቱ ስራ ላይም 580 ሺህ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ መሆናቸውንም ገልፀዋል።

የምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ አርሶ አደር ገለታ ውሉ ፤ላለፉት ሶስት አመታት በአቮካዶ ምርት ላይ በመሳተፍና የባለሙያዎችን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ ምርትና ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንዳስቻላቸው ይገልፃሉ።

በሁለት ሔክታር መሬት ላይ በክላስተር አቮካዶን በማልማትም የተሻለ ምርት ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆኑን ነው የሚገልጹት።

ሌላኛው አርሶ አደር አቶ ታሪኩ ነጋሳ በክላስተር የተለያዩ ፍራፍሬዎችን እያመረቱ እንደሚገኙ ገልፀው በዚህም ከራሳቸው አልፈው ለአካባቢው አምራች አርሶ አደር ልምድ እያካፈሉ መሆኑን ገልጸዋል።


ምርቱም ከምግብ በዘለለ በገቢ ምንጭነት እየተጠቀሙበት መሆኑን ነው የሚገልጹት።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026