የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በደብረ ብርሃን ከተማ የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተጠቃሚ አድርገውናል

Jul 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረብርሃን፤ ሐምሌ 13/2018(ኢዜአ)፦ በደብረ ብርሃን ከተማ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ዘላቂ ተጠቃሚነታችንን ያረጋገጡ ናቸው ሲሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ።

ከደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ በለጡ አስፋው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በከተማዋ የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በትኩረት መሰራታቸው ተጠቃሚ እንድንሆን አድርጎናል ብለዋል።

በተለይም ወንጀል ይፈፀምባቸው የነበሩ አካባቢዎችን በማልማት ውብ፣ ሳቢና ማራኪ የመዝናኛ ስፍራ እንዲሆን መደረጉ በተሻለ መንገድ ነዋሪውን ተጠቃሚ ለማድረግ ያስቻሉ ናቸው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅትም የከተማዋን አድገት በሚያፋጥኑ የልማት ስራዎች ላይ በጉልበት፣ በገንዘባቸው እና በእውቀታቸው በመሳተፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸዋል።

ሌላው የከተማዋ ነዋሪ አቶ ሠይድ ማሩ በበኩላቸው፤ በከተማው የተካሄዱ የመንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድልን የፈጠሩ ናቸው ብለዋል።

የተገነቡ የመሰረተ ልማቶች የአገልግሎት ጊዜያቸው እንዲረዝም የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር የመጠበቅና የመንከባከብ ስራ እየሰሩ መሆኑን ነው ያመለከቱት።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሽት በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ የልማት ስራዎች ከተማዋን የኢንዱስትሪ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ማእከል እንድትሆን ያስቻሉ ናቸው።


በዚሁ ወቅት ሰላምን ከማስጠበቅ ጎን ለጎን ህብረተሰቡ የተሳተፈበት የ75 ኪሎ ሜትር የጠጠርና ሶስት ኪሎ ሜትር የኮብል ስቶን መንገዶች መገንባታቸውን አስረድተዋል።

በተለይም በከተማዋ የተገነባው የሶስት ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ሥራ ደረጃውን የጠበቀ የእግረኛና የሳይክል መንገዶችን ጨምሮ የመዝናኛ እና የአረንጓዴ ስፍራዎችን ያካተተ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የቴሌኮሙኒኬሽንና የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ የተገነባ በመሆኑ ለከተማዋ እድገትና ለህዝቡ ተጠቃሚነት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ተናግረዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ19 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፈጠሩን ጠቁመው በአዲሱ በጀት ዓመትም ከዚህ የላቀ ስራ ለመስራት በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026