የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋን በራስ አቅም ለመቋቋም ርብርብ እየተደረገ ነው

Jul 21, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ማርቆስ ፤ ሐምሌ 14/2018 (ኢዜአ) ፦በምስራቅ ጎጃም ዞን ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋምና በምግብ ራስን ለመቻል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የዞኑ አደጋ መከላከልና ስራ አመራር ተጠሪ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሾመ መኮነን ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በምግብ ራስን ለመቻል መንግስት ያስቀመጠውን አቅጣጫ ተግባራዊ በማድረግ በኩል ሁሉን አቀፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

በተለይም በአካባቢው ዝናብ አጠር ፣ ጎርፍና በረዷማ በሆኑ ወረዳዎች ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲገጥም በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለዚህም በተያዘው የክረምት ወቅት ከሁለት ሺህ 400 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት የሚያጋጥሙ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮችን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በሁሉም ወረዳዎች ከ400 ሄክታር በላይ መሬት ደጋግሞ የታረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 40 ሄክታር የሚሆነውን በስንዴና በጤፍ ዘር መሸፈኑን ገልጸዋል።

ከዚህም ከ96 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ነው ያስረዱት።

ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግም ከሰባት ሺህ 500 ኩንታል በላይ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በማሰራጨት አርሶ አደሩ ጥቅም ላይ እንዲያውለው መደረጉን አብራርተዋል።

የደጀን ወረዳ የየትኑራ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መኩሪያው ፈለቀ፤ ከተረጅነት ለመላቀቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን አስረድተዋል።

በቀበሌያቸውም በምግብ ራስን ለመቻል የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን ለመሙላት በሚደረገው ጥረት ውስጥ በመሳተፍ ለዚሁ የተዘጋጀውን መሬት የማረስ ስራ ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ገልፀዋል።

የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ነገሰ ኑሬ በበኩላቸው ፤በቡድን በመሆን በምግብ ራስን ለመቻል የተለየውን መሬት በማረስ ለዘር ዝግጁ አድርገው እየተጠባበቁ መሆኑን ገልፀዋል ።

ማሳውን በዘር ከመሸፈን ባለፈ በአረም፣ ሰብሉን ከተባይ በመከላከልና ከመንከባከብ ጀምሮ እስከ ሰብል ስብሰባው ድረስ በመሳተፍ ድርሻቸውን እንደሚወጡ አስረድተዋል።

በዞኑ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በምግብ ራስን ለመቻል በተደረገው እንቅስቃሴ ከ104 ሚሊዮን ብር በላይ ከማህበረሰቡ በማሰባሰብ ጥቅም ላይ ማዋል መቻሉን ከተጠሪ ጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026