የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ምክር ቤቱ ለ2019 በጀት ዓመት 45 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ

Jul 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ታርጫ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት 45 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ።

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን በታርጫ ከተማ እያካሄደ ነው።

የክልሉ ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የኋላሸት በላይነህ፤ የክልሉ መንግስት የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 45 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን 231 ሺህ 974 ብር መሆኑን ለጉባኤው በዝርዝር አቅርበዋል፡፡


በጀቱ ከክልሉ ከሚሰበሰብ ገቢና ከፌደራል መንግስት ድጋፍ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል ።

የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ በበኩላቸው፤ በጀቱ በድህነት ቀናሽ ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።


በተጨማሪም ማህበራዊ አገልግሎትን ለማጠናከር ፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የኢንዱስትሪና የኤክስፖርት ምርቶች እንዲሁም መስኖ ልማት ጨምሮ ግብርና ስራዎችን ለማስፋትና ለፕሮጀክቶች ማጠናቀቂያ የሚውል መሆኑን አመላክተዋል።

ምክር ቤቱ በቀረበው የክልሉ የ2019 ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026