የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

ዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና አስተዳደር ለጠንካራ ኢኮኖሚ ግንባታ ሚናውን እየተወጣ ነው

Jul 29, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅማ ፤ሐምሌ 21/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት ዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና አስተዳደር አገልግሎት ትልቅ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ።

በጅማ ከተማ በዛሬዉ ዕለት የገጠር ካዳስተር ስፍር የመዝጊያ ፕሮግራም ተካሂዷል።


በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ ፣ የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ሀላፊ መሠረት አሰፋ እና ሌሎችም የዞን እና የወረዳ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ነመራ ቡሊ በወቅቱ እንደገለጹት ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት በሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ የመሬት አስተዳደር ትልቅ ሚና አለው።

ይህንን ከግብ ለማድረስ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር አገልግሎት ተግባራዊ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በክልሉ የተሰራው የካዳስተር ስራም ተጨባጭ ለዉጥ ማምጣቱን ጠቅሰዋል።

ዘመናዊ የመሬት አያያዝ እና አስተዳደር አገልግሎትን በማሳካት ወደ ትልቅ የገቢ ምንጭ የመቀየር ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመው ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ።


የኦሮሚያ መሬት ቢሮ ሀላፊ መሠረት አሰፋ በበኩላቸዉ የመሬት ካዳስተር አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን አስገኝቷል ብለዋል።

ከዚህ ውስጥ አርሶ አደሮችን ወደ ኢንቨስትመንት ማሸጋገር ፣ የመሬት ብክነትን ማስቀረትና ግልፅና ቀልጣፋ አገልግሎትን መስጠት እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል ።

በክልሉ በ21 ዞኖች ለ4 ሚሊዮን 69 ሺህ 179 አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መሰጠቱን አስታውቀዋል።


የጅማ ዞን አስተዳዳሪ ቲጃኒ ናስር በበኩላቸው የካዳስተር አገልግሎት የዞኑን ገቢ ከማሳደግ በተጨማሪ ኢንቨስትመንትን እያጠናከረ ነዉ ብለዋል።

ግልፅነትን በማስፈን ሀብትን በአግባቡ መጠቀም ያስቻለ መሆኑንም አመልክተዋል።

የጅማ ዞን መሬት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አብዱልሀሚድ ሀጂ በዞኑ የተጀመረዉ የመሬት ካዳስተር አገልግሎት በርካታ ጠቀሜታ ማስገኘቱን ጠቁመው በ20 ወረዳዎች እና በ513 ቀበሌዎች መሬት በካዳስተር መሰፈሩን ተናግረዋል።

በዚህም ለ397 ሺህ 647 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መሰጠቱን ገልፀዋል።

የካዳስተር አገልግሎት የአርሶ አደሩን የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር በማሻሻል ግንዛቤን ማሳደጉንም አክለዋል።


በጅማ ዞን የሰኮሩ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ዝናብ አባ ጎጀም ሁለት ሄክታር መሬታቸዉ ተሰፍሮ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማግኘታቸዉን ተናግረዉ አገልግሎቱ መሬታቸውን በአግባቡ ለማስተዳደር እንዳገዛቸዉ ጠቅሰዋል።


ሌላዉ የሊሙ ሰቃ ወረዳ ነዋሪ አርሶ አደር ፋሪስ መሀሙድ መሬት ወደ ካዳስተር መግባቱ ከዚህ ቀደም በአካባቢያቸዉ በባለቤትነት ዙሪያ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን መፍታቱን ገልፀዉ የይዞታ ማረጋገጫ በማግኘቴ ተደስቻለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026