🔇Unmute
ባህር ዳር ፤ነሐሴ7/2018 (ኢዜአ)፡- ከአማራ ክልል የቅባትና ጥራጥሬ ምርቶችን ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ559 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ገቢ መገኘቱን የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው የሰብልና የኢንዱስትሪ ምርቶች ግብይት ዳይሬክተር አቶ ልንገረው አበሻ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ወደ ውጭ ተልከዋል።

ወደ ተለያዩ ሀገራት ከተላኩት የግብርና ምርቶች ውስጥ ከ1 ሚሊዮን 942 ሺህ ኩንታል በላይ ሰሊጥና ኑግ እንደሚገኙበት የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ ቀሪው ደግሞ የቦሎቄ፣ የአኩሪ አተር፣ የማሾና የቡና ምርቶች መሆናቸውን አመልክተዋል።
በበጀት ዓመቱ ወደ ውጭ ከተላኩ የቅባት፣ የጥራጥሬና የቡና ምርቶች በአጠቃላይ ከ559 ሚሊዮን 880 ሺህ 84 የአሜሪካ ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም ተናግረዋል።
ምርቶቹ ከተላኩባቸው ዋና ዋና አካባቢዎች መካከል አውሮፓ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ ህንድ፣ ሩቅ ምስራቅ እና የእስያ ሀገራት እንደሚገኙበት ጠቁመዋል።
በአዲሱ የበጀት ዓመትም የተሻለ ምርት በጥራትና በብዛት አምርቶ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከዘርፉ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ለማሳደግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።
በ2016/2017 የበጀት ዓመት ከክልሉ ከ6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የቅባትና የጥራጥሬ ምርቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት መላካቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ጊምቢ፣ ነሐሴ4/2018 (ኢዜአ) ፡-በምዕራብ ወለጋ ዞን እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ተጨማሪ የገቢ ም...
Aug 11, 2026
ሰመራ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ) ፦ በአፋር ክልል የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል ...
Aug 10, 2026
ወልቂጤ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ በፍራፍሬ እና ቅመማ ቅመም ልማት ላይ መሰማራታችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታችንን ለማሳደግ አስችሎናል ሲሉ የጉራጌ ዞን አርሶ ...
Jul 29, 2026
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ የራሷን ዘላቂና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ በመገንባት ዓለም አቀፋዊ ተደማጭነቷንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን ማጎልበ...
Jul 29, 2026