🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 13/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያዊያን በርካታ ግድቦችን የመገንባት አቅሙም ዝግጁነቱም እንዳላቸው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) ተናገሩ።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በዋናነት የግድቡን ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ በማስተባበር ግንባታው በስኬት እንዲጠናቀቅ ያደረገ ተቋም ነው።
የጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር)፤ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የዓባይ ውሃ ፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ለዘመናት የቆየ የተዛባ አረዳድን የቀየረ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።
ግድቡ የትኛውንም ሀገር እንደማይጎዳና ይልቁንም ቀጣናውን በኢነርጂ እያስተሳሰረ መሆኑ በተግባር መረጋገጡን ጠቅሰዋል።
ነገር ግን ግብጽ ይህንን እውነታ በመካድ አሁን ላይ የቀደመ በጩኸት የማደናገር ተግባሯን በስፋት እያከናወነች መሆኑን ተናግረዋል።
ዓባይ የተፋሰሱ ሀገራት በትብብር የሚጠቀሙት ሃብት እንጂ የግብጽ የግል ንብረት አይደለም ያሉት አረጋዊ (ዶ/ር)፤ከዚህ አኳያ የግብጽ የማደናገር ዘመቻ ሊቆም ይገባል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ ዋነኛ ዓላማ በትብብር ማደግ መሆኑንም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያዊያን በትብብር ምን ማሳካት እንደሚችሉ በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ማሳየታቸውን አንስተው፤ በቀጣይም በርካታ ግድብ የመገንባት አቅሙም ዝግጁነቱም አላቸው ብለዋል።
በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅት ሕዝብን በማስተባበር ረገድ በርካታ ጠቃሚ ልምድ መገኘቱንም ተናግረዋል።
ይህ ልምድ በቀጣይ ለሚከናወኑ መሰል የልማት ስራዎች ትልቅ ግብዓት መሆኑንም አብራርተዋል።
ጋምቤላ፤ ነሀሴ 12/2018 (ኢዜአ)፡- የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈፀሚያ ከ18 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፀደቀ። ...
Aug 19, 2026
ጂንካ፤ ነሐሴ 12/2018(ኢዜአ) ፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ አርብቶ አደሮችን ህይወት በዘላቂነት ለመለወጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ስኬታማ መሆናቸውን...
Aug 19, 2026
ጊምቢ፣ ነሐሴ4/2018 (ኢዜአ) ፡-በምዕራብ ወለጋ ዞን እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ተጨማሪ የገቢ ም...
Aug 11, 2026
ሰመራ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ) ፦ በአፋር ክልል የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል ...
Aug 10, 2026