የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን ወደ ኢንቨስተርነት የማሸጋገር ስራ ውጤት እያመጣ ነው

Sep 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሸገር ፤ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፡- በሸገር ከተማ አርሶ አደሩን ከባህላዊ የአሰራር ዘይቤ በማላቀቅ ወደ ኢንቨስተርነት የማሸጋገር ስራ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን የኦሮሚያ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ጉዬ ገለጹ።

የሸገር ከተማ የገበሬዎች ቀን «ዘመናዊ ገበሬና ዘመናዊ ግብርና ለአጠቃላይ ብልፅግና» በሚል መሪ ቃል በከተማው ሱሉልታ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግም የባዛር እና ኤግዚቢሽን መርሃ ግብር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የግብርና ምርቶች፣ የግብርና ማሽነሪዎችና ግብዓቶች ለእይታ ቀርበዋል።


በመርሃ ግብሩ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ጉዬ፤ ሸገር በጥቂት ዓመታት ቆይታ ውስጥ ታላላቅ ስኬቶችን እያስመዘገበች መሆኗን ገልጸዋል።

የሸገር ከተማ ከተመሰረተች በኋላ በተለይም በከተማ ግብርና የተሰማሩ አርሶ አደሮችን የግብርና ቴክኖሎጂዎች፣ የግብዓት አቅርቦት፣ ሙያዊ ድጋፍና መሰል ጉዳዮችን በማቅረብ ውጤታማ እንዲሆኑ በተሰራው ስራ ውጤት እየተገኘ እንዳለ አመልክተዋል።

በመሆኑም በከተማ አስተዳደሩ አርሶ አደሩን ከባህላዊ የአሰራር ዘይቤ በማላቀቅ ወደ ኢንቨስተርነት የማሸጋገር ስራ ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል።

የሸገር ከተማ ከንቲባ ተሾመ አዱኛ(ዶ/ር) በበኩላቸው በመደመር እሳቤ ባለፉት ዓመታት ከተማዋን የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ ከተከናወኑት ተግባራት ጎን ለጎን የአርሶ አደሩንና የከተማዋን ሕዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰራው ሥራ በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል።

ከተማው የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም በመገንባትና በማሳደግ በጋራ የምታድግ ከተማ መሆኗንም ገልጸዋል።


የእርሻ ሜካናይዜሽንና ቴክኖሎጂን በማስፋት፣ የግብርና ግብአቶችን በወቅቱ በማቅረብ እንዲሁም የአርሶ አደሩን የሥራ ባህል በመለወጥ በርካታ አርሶ አደሮችን ወደ ኢንቨስትመንት ማሸጋገር መቻሉንም ለአብነት አንስተዋል።

እንዲሁም የንግድ ቦታዎችንና የተለያዩ ሁኔታዎችን በማመቻቸትና የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ በርከታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

በከተማው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የግብርና ክላስተር አስተባባሪ አቶ ግርማ ሀይሉ እንደገለጹት፤ አስተዳደሩ ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ቀደም ሲል ከመሬቱ ይፈናቀል የነበረው አርሶ አደር አሁን በመሬቱ ላይ ባለቤት ሆኖ በተለያዩ ዘርፎች በመደራጀት ምርትና ምርታማነቱን እያሳደገ ይገኛል።


በመደመር መንግስት ባለፉት ዓመታት የተሰሩ ሥራዎች የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስብራቶችን መታደግ መቻሉንም አንስተዋል።

በዚህም አርሶ አደሩንና ግብርናውን በማዘመን የከተማዋን የዕድገት ጉዞ ለማሳደግና አጠቃላይ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን የዛሬው መርሃግብር ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ማልማት ተጀምሯል

ደብረ ብርሃን ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በበጋ መስኖ ከ76 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱ...

Oct 20, 2026

በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል

ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የ...

Oct 9, 2026

የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ  የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ማንሰራራት አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል የሚገነባው የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ...

Sep 30, 2026

የእጣንና ሙጫ ደኖችን ለመንከባከብ የማህበረሰብ አቀፍ የደን ጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ ነው

ገንዳውኃ፣ መስከረም 9/2019 (ኢዜአ):- የእጣንና ሙጫ ደኖችን በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማህበረሰብ አቀፍ የጥበቃ ሥራዎች እየተካሔደ መ...

Sep 20, 2026